ስምምነት / ዲያጎ ሲሞኔ የአትሌቲኮ ማድሪድ ቆይታቸውን እስከ 2020 ድረስ አራዘሙ

ዲያጎ ሲሞኔ የሶስት አመት አዲስ የውል ስምምነት በመፈራረም በአትሌቲኮ ማድሪድ ያላቸውን የአሰልጣኝነት ቆይታ እስከ 2020 ድረስ አራዝመዋል። 

የአትሌቲኮው አለቃ ከአመት በፊት በስፔኑ ክለብ እስከ 2020 የነበራቸው ቆይታ በሁለት አመት እንዲያጥር ተደርጎ እስከ 2018 ብቻ እንዲሆን መደረጉ ከክለቡ ለመለያየት መቃረባቸውን የጠቆመ ተደርጎ ቢታይም የሲሞኔ ኮንትራት ዳግመኛ ወደቀደመ የውሉ ጊዜ እንዲመለስ ተደርጓል።

በታህሳስ 2011 የአትሌቲኮን የአሰልጣኝነት ሹመት ያገኙት የ 47 አመቱ ሰው በተጫዋችነት ላገለገሉበት ክለብ ላሊጋ፣ ኮፓ ዴላሬይ እና ኢሮፓ ሊግን የመሰሉ አምስት ትልልቅ ዋንጫዎች ማስገኘት የቻሉ ሲሆን ለክለቡ ያላቸውን ታማኝነትም የውል ስምምነታቸውን በማራዘም ማሳየት ችለዋል።

አትሌቲኮ በሲሞኔ አሰልጣኝነት ስር ለሁለት ጊዜያት በ 2014 እና በ 2016 ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ክብር መብቃቱ የማይረሳ ሲሆን የስፔኑ ክለብ በቀድሞው ተጫዋቹ የአምስት አመታት የአሰልጣኝነት ዘመን በላሊጋው ከምርጥ ሶስት ውጪ ጨርሶ አያውቅም።

አትሌቲኮ እስከ መጪው የፈረንጆች አዲስ አመት ድረስ በተጣለበት የዝውውር እገዳ ምክንያት ቡድኑን በአዳዲስ ተጫዋቾች ማጠናከር ባይችልም የዋንዳ ሜትሮፖሊቲያን ስታዲየም ቆይታውን መስከረም ማላጋን በአዲሱ ሜዳው በሚያስተናግድበት ጨዋታ አሀዱ ብሎ ይጀምራል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s