አቤቱታ / ሊቨርፑል በሩሲያው ክለብ ላይ የዘረኝነት ክስ መሰረተ

ሊቨርፑል ከስፓርታክ ሞስኮ ጋር ባደረገው የዩኤፋ ወጣቶች ሊግ ጨዋታ ወቅት በ18 ዓመቱ የክንፍ ተጫዋቹ ቦቢ አደካንዬ ላይ የዘረኝነት የስድብ ጥቃት የደረሰበት መሆኑን ተከትሎ በሩሲያው ክለብ ላይ ለአውሮፓ ህብረት እግርኳስ ማህበር መደበኛ ክስ መስርቷል።

ትውልደ ናይጄሩያዊው እና የሆላንድ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቹ አደካንዬ በሞስኮ በተደረገው የማክሰኞ ዕለቱ የአውሮፓ ህብረት የወጣቶች ሊግ ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ተቀይሮ ሲገባ የዘረኝነት ስድቦችና ምልቶች ጥቃት ተፈፅሞባታል የሚል ክስ ቀርቧል። 

የሊቨርፑል የወጣቶች ማሰልጠኛ ዋና ኃላፊ የሆኑት አሌክስ ኢንግልትሮፕ እና የማስለጠኛው የስራ ባልደረቦቹ እምነት ከሆነ በስፓርታክ ማሰልጠኛ ላይ ለተከሰተው ድርጊት የእነሱም ትዝብት ለአውሮፓ የህግ አማራር አካል በቀረበው አቤቱታ ላይ እንደአይን እማኝ ማስረጃ ይቀርባል።

ወጣቱ ተጫዋች በሩሲያ የ2ለ1 ሽንፈት በደረሰበት የስቴቨን ጄራርዱ ቡድን በ59ኛው ደቂቃ ተቀይሮ የገባ ሲሆን፣ ክለቡም ላቀረበው ክስ ከአውሮፓ ህብረት እግርኳስ ማህበር ምላሽ እየጠበቀ ይገኛል። 

ስፓርታክ በኦትክርይቲዬ አሬና 1ለ1 ባጠናቀቀው ጨዋታ ላይ ደጋፊዎቹ “ዩኤፋ ማፊያ” የሚል አርማ እንግበው በመታየታቸው ፣ ፈርናንዶ የቅጣት ምቱን ግብ ካስቆጠረ በኋላ የጭስ ቦምብ በማቀጣጠላቸው እንዲሁም የስታዲየም መወጣጫ ደረጃዎችን በመዝጋት ሌላ ሶስት ክሶች ከፊታቸው ይጠብቋቸዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s