ሲቲ ካፕ / የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ድልድል ማክሰኞ ይወጣል

8 የፕሪሚየር ሊጉ እና የከፍተኛ ሊጉ ተወዳዳሪ ክለቦች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው 12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር የምድብ ድልድል እና መርሀ ግብር የፊታችን ማክሰኞ ጠዋት እንደሚወጣ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል፡፡

14657399_586425208232781_1773926396690374867_n

የከተማው ፌዴሬሽን እስካሁን የተሳታፊ ክለቦችን ማንነት ይፋ ባያደርግም  ሁሉንም ተሳታፊ ክለቦች ነገ (ሰኞ) ረፋድ ለመገናኛ ብዙሀን ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እስካሁን ኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ ኢትዮ ኤሌክትሪከ እና ደደቢት መሳተፋቸው እርግጥ የሆነ የከተማው ክለቦች ሲሆኑ ከክልል ደግሞ ፋሲል ከተማ እና አዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በተጋባዥነት እንደሚሳተፍ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ተሰምቷል፡፡

በአዲስ አበባ ስቴዲየም ከመስከረም 27 እስከ ጥቅምት 12 በሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር አንደ ከዚህ ቀደሞቹ ውድድሮች የስፖንሰር ስያሜ ይኑሩው አይኑረው እስካሁን ይፋ የሆነ ነገር ባይኖርም ማክሰኞ  ጠዋት (ሰኞ) በኢትዮጵያ ሆቴል በሚኖረው እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ላይ ግን ፌዴሬሽኑ ስለ 2010 የከተማው ዋንጫ በርካታ ነገሮች ይዞ ብቅ እንደሚል እየተነገረ ይገኛል፡፡

የዚህ ውድድር ያሳለፍነው አመት አሸናፊ ኢትዮአሌክትሪክ ሲሆን በወቅቱም በኢብራሂም ፎፋና ብቸኛ ግብ ፈረሰኞቹን ኢትዮኤሌክትሪክ 1-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s