ማገገም/ ዝላታን ኢብራሂሞቪች በጥቅምት መጨረሻ ልምምድ ይጀምራል

Image result for Zlatan Ibrahimovic 2017 training

ባሳለፍነው አመት ማንችስተር ዩናይትድ በኢሮፓ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ ከአነድርሌክት ጋር በነበረው ፍልምያ ከባድ የጉልበት ጉዳት የገጠመው ዝላታን ኢብራሂሞቪች ጉዳቱ እስከ 2017 መጨረሻ ከሜዳ ያርቀዋል ቢባልም በጥቅምት መጨረሻ ልምምድ ሊጀምር እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በ46 ጨዋታዎች 28 ግቦችን በሁሉም ውድድሮች በማስቆጠር ማንችስተር ዩናይትዶች የኮምዩኒቲሺልድ የኢሮፓ ሊግ እና የኢኤፍኤል ዋንጫ አሸናፊ እንዲሆኑ ማድረግ ያስቻለው የ35 አመቱ አጥቂ በጅምናዚየም ልምምድ ከጀመረ የሰነበተ ሲሆን ከጉዳቱ በፍጥነት ማገገሙን ተከትሎም በጥቅምት ወር መጨረሻ ከክለቡ ጋር ልምምድ እንደሚጀመር ዘሰን አስነብቧል፡፡

ተጫዋቹ  በቶሎ ወደ ሜዳ እንደማይመለስ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ ከውድድር ዘመኑ ቀደም ብለው የነበረ ተናግረው የነበረ ሲሆን አሁን እየወጡ ባሉት መረጃዎች መሰረት ግን ስዊዲናዊው የቀድሞ የባርሴሎና ፊት አውራሪ ለሳምንታት በካሪንግተን በግሉ ልምምዱን በጅምናዚየም ከሰራ በኋላ በውድድር ዘመኑ አስፈሪ ሆኖ የመጣውን የማንችስተር ዩናይትድ ስብስብ በመቀላቀል ልምምዱን በይፋ በካሪንግተን ይጀምራል ተብሏል፡፡

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ስሙ የተላለፈው ግዙፉ አጥቂ ምን አልባትም የአካል ብቃቱ ጥሩ ከሆነ እና መጫወት የሚያስችለው ከሆነው በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ላይ ሊሰለፍ እንደሚችል ከወዲሁ እየተነገረ ይገኛል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s