ትችት / አሪያን ሮበን ካርሎ አንቼሎቲ ላይ ጠንካራ ትችት አቀረበ

አሪየን ሮበን በ ፓሪስ ሴንት ጄርሜይን 3-0 ከተሸነፉ በኋላ ከሀላፊነታቸው የተነሱትን ካርሎ አንቼሎቲን አጥብቆ ተቸ።

በነሀሴ 2016 ላይ ከፔፕ ጋርዲዮላ ተረክበው የባየርሙኒክ አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት ካርሎ አንቼሎቲ ከአንድ አመት በኋላ ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል።

አንቼሎቲ ባለፈው አመት የጀርመን ቡንደስሊጋን ዋንጫ ከባየርሙኒክ ጋር ቢያነሱም በቻምፕየንስ ሊጉ ገፍተው መጓዝ ባለመቻላቸው ብዙም ድጋፍ ማግኘት ሳይችሉ ቀርቷል።

አንዳንድ መረጃዎች አሰልጣኙ ከሀላፊነታቸው ለመነሳት አንዳንድ ተጫዋቾች አድማ እንደመቱባቸው ሲነገር ቆይቷል።

የቡድኑ የመስመር ተጫዋች የሆነው አሪያን ሮበንም በይፋ ካርሎ አንቼሎቲ ላይ ጠንካራ ትችት አቅርቧል።

ተጫዋቹ ትችቱን ያቀረበው በአሰልጣኙ የአሰለጣጠን መንገድ ላይ ሲሆን “ካርሎ አንቼሎቲ ከሚሰጡት ስልጠና ልጄ የሚሰለጥንበት የወጣት ቡድን የተሻለ ስልጠና ይሰጣል።” በማለት ነው።

አንቼሎቲ ቀጣይ ማረፊያቸው ባይታወቅም ምናልባትም ወደ ቀድሞ ክለባቸው ኤሲ ሚላን የሞመለሱበት እድል እንደሚኖራቸው እየተነገረ ይገኛል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s