አትሌቲክስ/ የ2017 የአመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት እጩዎች ይፋ ተደረጉ

በየአመቱ የአለም የአመቱ ምርጥ አትሌቶችን እየመረጠ የሚሸልመው አለም አቀፉ የአትሌቲክስ አስተዳዳሪ አካል ለአመቱ ምርጥነት የታጩ አትሌቶችን በሁለቱም ፆታዎች ይፋ ያደረገ ሲሆን የፌስቡክና የትዊተር ተጠቃሚዎች በምርጫው ላይ ተሳታፊ የሚሆኑበት አሰራር እንደተዘረጋ አሳውቋል፡፡

ማህበሩ በአውሮፓውያን የጊዜ ቀመር ህዳር 24 ቀን 2017 ላይ አሸናፊ አትሌቶችን ይፋ እንደሚያደርግ የገለፀ ሲሆን የመጨረሻ ሶስት እጩዎችን ከመለየቱ በፊት በቅድመ እጩነት የመረጣቸውን ሃያ አትሌቶች ይፋ አድርጓል፡፡ 

ማህበሩ በሁለቱም ፆታዎች አስር አስር አትሌቶችን መርጦ ያሳወቀ ሲሆን ኢትዮጵያ በሴቶቹ ዝርዝር ውስጥ በተካተተቸው አልማዝ አያና ተወክላለች ፡፡

በሴቶች የምርጥ አትሌትነት እጩዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

° አልማዝ አያና (ETH)

° ማሪያ ላስቲካኒያ (ANA)

° ሄለን ኦቢሪ (KEN)

°  ሳሊ ፒርሰን (AUS)

° ሳንድራ ፒርኮቪች (CRO)

° ብሪትኒ ሬስ (USA)

° ካስተር ሴሚኒያ (RSA)

° ኢካተርኒ ስቴፋንዲ (GER)

° ናፊሳቱ ቲያም (BEL)

° አኒታ ውሎድራዚ (POL)

በወንዶች የምርጥ አትሌትነት እጩዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

° ሙታዝ ኢሳ ባርሺም (QAT)

° ፖል ፌጄክ (POL)

° ሞ ፋራህ (GBR)

° ሳም ኬንድሪክስ (USA)

° ኤልያህ ማናንጎይ (KEN)

° ሉቮ ማንዮንጋ (RSA)

° ኦማር ማክሊዩድ (JAM)

° ክርስቲያን ቴይለር (USA)

° ዋይድ ቫን ኔዬክረክ (RSA)

° ጆን ቬተር (GER) ናቸው፡፡

ሶስቱን የመጨረሻ እጩዎች ለመለየት የሚደረገው ምርጫ ሃምሳ በመቶ በአትሌቲክስ ማህበሩ ካውንስል ምርጫ የሚደረግ ሲሆን “የአትሌቲክስ ማህበሩ ቤተሰቦች” እና የማህበራዊ ሚድያ ተከታዮች ድምፅ ሃያ አምስት በመቶ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ ማህበሩ እያንዳንዱን አትሌት በፌስቡክና በትዊተር ገፁ የሚያስመርጥበት አሰራር በቅርቡ እንደሚለቀቅና አትሌቶቹ የሚያገኙት የ ላይክ (Y) መጠን እንደድምፅ እንደሚቆጠር ከማህበሩ ድረ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s