እጩ / ​የአለም አቀፍ የአትሌቲክ ፌዴሬሽን የ 2017 የአለም ምርጥ  እጩ አትሌቶችን አሳወቀ

የአለም አቀፍ የአትሌቲክ ፌዴሬሽን ማህበር የ 2017 የአለም ምርጥ አትሌት ለመምረጥ በሁለቱም ጾታዎች 10 እጩ አትሌቶች ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያም በአንድ አትሌት ተወክላለች።

 እጩ ሆነው የቀረቡ አትሌቶችን በሶስት አይነት መንገዶች ድምጽ የመስጠት ሂደት ይደረጋል።የመጀመሪያው የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኮሚቴ እና ቤተሰቦች በኢሜል የሚያደርጉት ምርጫ ሲሆን

ደጋፊዎች ደግሞ በአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበራዊ ሚዲየ በሚያዘጋጀው የምርጫ ቅጽ(Platform) መሰረት ምርጫቸውን ያደርጋሉ።

ይህም የያንዳንዱ አትሌት ምስል በፌስበክ እና በትዊተር ላይ በመልቀቅ ሲሆን ደጋፊዎች ላይክ እና ፌቨራይትን በመጫን ምርጫውን ማድረግ ይችላሉ።

የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኮሚቴ የሚሰጠው ድምጽ 50% የሚይዝ ሲሆን የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ቤተሰቦች እና የህዝብ ድምጽ እያንዳንዱ 25% ድርሻ ይኖረዋል።

የድምጽ ምርጫው የመጨረሻ እለትም በፈረንጆቹ ጥቅምት 16 ሲሆን በምርጫው ከፍተኛ ድምጽ ያገኙ ከሁለቱም ጾታዎች ሶስት ሶስት አትሌቶች በአጠቃላይ ስድስት አትሌቶች ይፋ ይደረጋሉ።

አርብ ህዳር 24 በሞናኮም በቀጥታ ስርጭት በሁለቱም ጾታዎች የአመቱ ምርጥ አትሌቶች ይፋ ይደረጋሉ።

እጩ ውስጥ የገቡ

በወንዶች

1) ሙታዝ ኢሳ ባርሺም (ኳታር)

2) ፓውል ፋጅዴክ (ፓላንድ)

3) ሞሀመድ ፋራህ (እንግሊዝ)

4) ሳም ኬንድሪክስ(አሜሪካ)

5) ኢሊጃ ማናንጎይ (ኬኒያ)

6) ሉቮ ማንዮንጋ (ደ/አፍሪካ)

7) ኦማር ማክሊዎድ(ጃማይከ)

8) ክርስቲያን ቴይለር (አሜሪካ)

9) ዋይድ ቫን ኒክርክ (ደ/አፍሪካ)

10) ጆሀንስ ቪተር (ጀርመን)

በሴቶች

1) ማሪያ ላሲትስኪን (ራሺያ)

2) ሄለን ኦብሪ (ኬኒያ)

3) ሳሊ ፒርሰን (አውስትራሊያ)

4) ሳንድራ ፔርኮቪች(ክሮሺያ)

5) ብሪትኒ ሪዝ (አሜሪካ)

6) ካስተር ሴምኒያ (ደ/አፍሪካ)

7) ኢካቴሪኒ እስቲፋኒዲ(ግሪክ)

8) ናፊሳቱ ታያም (ቤልጄም)

9) አኒታ ውሎዳርዚክ(ፓላንድ)

10) አልማዝ አያና(ኢትዮጵያ) ናቸው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s