የአዲስ አበባ ዋንጫ/ በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ የሚሳተፉ ክለቦች ተለይተው ታወቁ

በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በየአመቱ የሚካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) ከመስከረም 27 እስከ ጥቅምት 12 በአዲስ አበባ ስቴዲየም የሚካሄድ ሲሆን በውድድሩ የሚሳተፉ ክለቦችን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል፡፡

ለ12ኛ ጊዜ የሚካሄደው ውድድሩ ስምንት ክለቦችን የሚያሳትፍ ሲሆን ስድስት የከተማው ክለቦች እንዲሁም ሁለት ተጋባዥ ክለቦች ተሳትፎ የሚያደርጉበት ይሆናል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ደደቢት ፣ መከላከያ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ አዲሰ አበባ ከነማ ፣ አዳማ ከነማና ጅማ አባጅፋር የዘንድሮው ሻምፒዮና ተሳታፊ እንደሚሆኑ ፌዴሬሽኑ ያረጋገጠ ሲሆን የምድብ ድልድል የዕጣ አወጣጥ ሰነ ስርአቱም በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ሆቴል እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

በ2009 የተካሄደውን ውድድር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን በአጠቃላይ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ አራት ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን የበላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሶስት ሶስት ጊዜ ዋንጫውን ከፍ በማድረግ በቀጣይነት ተቀምጠዋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s