ጉዳት ያጋጠመው አልቫሮ ሞራታ ለምን ያህል ጊዜ ከጨዋታ ውጪ እንደሚሆን ታወቀ

የጡንቻ መሳሳብ ያጋጠመው አጥቂው አልቫሮ ሞራታ ለምን ያህል ከሜዳ እንደሚርቅ ዛሬ በስፔን ካምፕ ምርመራ ካደረገ በኋላ ታውቋል።

ቼልሲዎች በሜዳቸው ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ከመሸነፉቸው በተጨማሪ የአጥቂው አልቫሮ ሞራታን በጉዳት ማጣታቸው ይታወሳል።

ተጫዋቹ በጡንቻ መሳሳብ ጨዋታውን አቋርጦ ለመውጣት የተገደደ ሲሆን እስከዛሬ ድረስ ለምን ያህል ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ የታወቀ ነገር አልነበረም።

ነገርግን ዛሬ[ሰኞ] በስፔን ካምፕ ውስጥ በተደረገለት ምርመራ ተጫዋቹ ላይ የደረሰው የጡንቻ መሳሳብ የሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ በመሆኑ ጉዳቱ ለረጅም ሳምንታት ከሜዳ እንደማያርቀው ታውቋል።

በምርመራው ውጤት መሰረት ሞራታ ቢያንስ ለሁለት ሳምንታት ከሜዳ የሚርቅ ሲሆን ስፔን ከአልባኒያ እና ከእስራኤል ጋር ላለባት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውጪም መሆኑ ተረጋግጧል።

ዳኒ ካልቨሀል እና አንድሬስ ኢኒየስታም በጉዳት ከስፔን ብሄራዊ ቡድን ውጪ በመሆን አልቫሮ ሞራታን የተቀላቀሉ ሌሎች ተጫዋቾች ሆነዋል።

ሞራታ ወደ ቼልሲ ከተቀላቀለ በኋላ ቶሎ በመልመድ ምርጥ አቋሙን እያሳየ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት የኢንተርናሽናል ጨዋታዎች በመሆኑ ቼልሲዎች ተጫዋቹን ብዙም ሳያጡት ወደ ሜዳ እንደሚመለስላቸው ይጠበቃል።Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s