ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሽልማት ተበረከተ

በኬንያ በአስረኛው የዓለም አቀፍ የወጣቶች የአትሌቲክስ ሻምፒዮናና በአልጄሪያው አስራ ሶስስተኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች እና የልዑካን ቡድን አባላት የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ማበርከቱን የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ዛሬ (ማክሰኞ) ገልፅዋል ገልፅዋል።

ከኃምሌ 13-17፣ 2009 ዓ.ም በተካሄደው የኬንያው የታዳጊዎች ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ አራት ወርቅ፣ ሶስት ብር ፣ አምስት ነሃስ በድምሩ 12 ሜዳዮችን በማግኘት ከአፍሪካ ሁለተኛ እንዲሁም ከዓለም አምስተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶካችና ልዑከን በወጣትና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከክቡር አቶ ርስቱ እጅ ሽልማታቸዉን ተቀብለዋል።

በሌላ በኩል በአልጄሪያዋ ቴልሚስ ከተማ ከሰኔ 29 -ኃምሌ 2 ድረስ በተካሄደው አስራሶስተኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተካፍለው 13 የወርቅ፣ 13 የብርና 12 የነሃስ በድምሩ 39 ሜዳዮችን በማግኘት የአህጉሪቱ አንደኛ በመሆን ውድድራቸውን ላጠናቁቁ አትሌቶችና ልዑካን ቡድኑ አባላት ሽልማቶቻቸውን ከወጣትና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ እጅ ተቀብለዋል፡፡

በኬንያው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ላይ ተሳትፎ አድርገው የወርቅ፣ የብር የነሃስ ሜዳላዮችን ላመጡ አትሌቶች እንደቅደም ተከተላቸው የ25፣ የ20 እና የ15 ሺህ ብሮች ሽልማት ሲበረከትለቸው፣ በአልጄሪያው የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ የማዳይ አሸናፊዎች ደግሞ የ20፣ የ15 እና የ10 ሺህ ብሮች ተሸልመዋል።

ለእነዚህ ለአትሌቶቹና ለአትሌቲክስ ልዑከን ቡድኖች በአጠቃላይ 1.5 ሚ.ብር ለሽልማት ወጪ እንደተደረገም የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ገልፅዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s