ስንብት / አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት እና መቐለ ከተማ ተለያዩ

20106635_701331563390074_3970543044646203537_n

በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተካፋዮ መቐለ ከተማ ሊጉ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያይቷል፡፡ ክለቡ ዛሬ አመሻሽ በመቀለ ከተማ ላይ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ከአሰልጣኙ ጋር አህል ውሀው ማብቃቱን አሳውቋል፡፡

ከዲስፕሊን ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ እንዲታረሙ ብጠይቅም ሊታረሙ አልቻሉም ፡፡ በተጨማሪም በአዲግራት ከተማ የመስቀል ዋንጫ በሚል ሊካሄድ የነበረ የመቐለ ከተማ እና የወልዋሎ አዲግራት የፍጻሜ ጨዋታ በራሳቸው ፍቃድ መቐለ ከተማ  እንዳይሳተፍ ማድረጋቸው አስቆጥቶኛል ያለው ክለቡ ከአሰልጣኝ  ጌታቸው ዳዊት ጋር የተለያየበት ምክንያት አብራርቷል፡፡

በአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ምትክ መቐለ ከተማ እስካሁን በይፋ አዲስ አሰልጣኝ ያልሾመ ሲሆን  ምክትል አሰልጣኙ ጎይቶም ሀይለ  ግን ቡድኑን ሊመሩት እንደሚችሉ የኢትዮአዲስ ተባባሪ ዘጋቢ ከስፍራው ተናግሯል፡፡ ክለቡ አዲሱን አሰልጣኝም በቅርቡ እንደሚያሳውቅም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ይፋ አድርጓል፡፡

በ1990ዎቹ ለትግራዩ ጉና ንግድ   ተጫውተው ያለፉት አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት በ2007 ውልዋሎን በብሄራዊ  ሊግ ማሰልጠን የቻሉ ሲሆን በዛው አመት በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዶ በነበረ የብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ላይ ክለቡን እሰከ ምድብ ማጣሪያ ድረስ መርተዋል፡፡ አሰልጣኙ በ2008 ከደደቢት ጋር በፕሪሚየር ሊጉ እስከ ውድድር አመቱ አጋማሽ ድረስ በዋና አሰልጣኝነት መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን በ2009 ደግሞ መቐለ ከተማን በከፍተኛ ሊጉ በማሰልጠን ለ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማሳለፍ ችለዋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s