ቅርጫት ኳስ/ ሀዋሳ ከተማ እና ጎንደር ከተማ ከዞን 5 የቅርጫት ኳስ ሻምፒዪና ውጪ ሆኑ

Image result for Fiba Zone 5

በኡጋንዳ ከተማ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 5ኛው የዞን 5 ሀገራት ክለቦች ሻምፒዮና እንደቀጠለ ነው፡፡ ከ መስከረም 21-መስከረም 28 ድረስ በሚዘልቀው በዚህ ውድድር በወንዶች እና በሴቶች 20 ክለቦች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በዚህ የቅርጫት ኳስ ሻምፒዮናም ኢትዮጵያን በመወከል እየተወዳደሩ የሚገኙት  ሀዋሳ ከተማ እና ጎንደር ከተማ ክለቦች ባደረጓቸው የመጀመሪያዎቹ 2 የቅርጫት ኳስ ግጥሚያዎች ሸንፈት ማስተናገዳቸውን ተከትሎ ከውድድሩ መሰናበታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በካምፓላ ሎጎጎ የቤት ውስጥ ስቴዲየም እየተካሄደ በሚገኘው ውድድር ሰኞ ምሽት የዩጋንዳውን ፓወር ሲቲን የገጠመው ጎንደር ከተማ 111 ለ 31 በሆኑ ሰፊ ውጤት የተረታ ሲሆን የኡጋንዳው ፓወር ሲቲ ይህንን ድሉን ተከትሎ በ6 ነጥቦች ከወዲሁ ሩብ ፍጻሜውን ማለፉን አረጋግጧል፡፡ በአንጻሩ ጎንደር ከተማ ደግሞ ከምድቡ መውደቁን አረጋግጧል፡፡

ሲቲ ኦይልን በሁለተኛው ቀን ያገኘው ሀዋሳ ከነማም 111 ለ 41 ቅርጫት የተሸነፈ ሲሆን ይህ ሽንፈቱም 2ኛው መሆኑን ተከትሎ 1 ጨዋታ እየቀረው ከወዲሁ ከውድድሩ ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s