“ባርሴሎና ወደ ወደ እንግሊዝ ከመጣ ለፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ፈታኝ ነው”- አርሰን ዌንገር

Image result for Arsenal boss Arsene Wenger

የካታላን ከስፔን እንገንጠል ጥያቄ መበርታት እና ከዚያም አልፎ ወደ ህዘበ ውሳኔ መሄድን ተከትሎ በርካቶች የባርሰሎና የላሊጋ ቆይታ እንዴት ይሆን የሚል ጥያቄን እያስነሱ ይገኛሉ፡፡ የካታላኑ ክለብ ባሳለፍነው እሁድ ላስፓልማስን በረታበት ጨዋታም የእንገንጠል ጥያቄውን በመደገፍ በዝግ ስቴዲየም ተጫውቷል፡፡

ካታላን እውን ከስፔን ተገንጥላ ሯሷን የቻለች ሀገር ከሆነችም የባርሴሎና የላሊጋ ቆይታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይገባል፡፡ በዚህ የተነሳም ባርሴሎና የትኛውን ሊግ ይቀላቀላል የሚለው ነገር በስፋት እየተነሳ ይገኛል፡፡ አሰልጣኝ አርሰን ዌንገርም ብራይተን ሆቭን በሊጉ 2-0 ከረቱበት ጨዋታ በኋላ  ከዚሁ ጉዳይ ጋር  በተያያዘ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ  ባርሴሎና ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከመጣ ለሊጉ ክለቦች ፈተና ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ንግግራቸውን በቀልድ የጀመሩት ፈረንሳዊው አለቃ ጉዳዩን የካታላን ቋንቋ እየተማርኩ ነው በማለት በቀልድ የጀመሩ ሲሆን ባርሴሎና ሊጉን ተቀላቅሎ የሚጫወት ከሆነ ሊጉ ከከዚህ ቀደሙ በላይ ለሌሎች ክለቦች ፈተና ይሆናል ዋንጫዎች ማሸነፍ አስቸጋሪ ነው ሲሉ የባርሴሎና መምጣት ለሊጉ ክለቦች ከባድ ተግዳሮት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም ባርሴሎናው ፕሬዝደንት ጆሴፍ ባርቶሚዮ ባሳለፍነው ሰኞ እንደተናገሩት ከሆነ ደግሞ ካታላን ራሷን የቻለች ሀገር መሆን የምትችል ከሆነ ባርሴሎና የስፔንን ሊግ ለቆ ሊወጣ የሚችልበት እድል መኖሩን ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በዛሬው እለትም የካታላንን መገንጠል በመደገፍ የባርሴሎና ክለብ ሙሉ በሙሉ ልምምዱን ያልሰራ ሲሆን የታዳጊ እግርኳሰኞች ማምረቻ እንደሆነ የሚነገርለት ላማሲያም በተመሳሳይ በዛሬው እለት ዝግ ሆኖ እንደዋለ ተነግሯል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s