“ከጉዳቴ በፍጥነት ለማገገም እየሰራው ነው”- አልቫሮ ሞራታ

Morata will remain in Spain despite pulling out of the upcoming World Cup qualifiers against Albania and Israel

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲ በማንችስተር ሲቲ 1-0 በተረታበት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ በብሽሽት ጉዳት ከሜዳ ተቀይሮ የወጣው አልቫሮ ሞራታ ሀገሩ ስፔን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ወሳኝ ጨዋታዎች ላይ አለመሰለፉ ቢረጋገጥም  ከ 10 ቀናት በኋላ በሊጉ ቼልሲ በሴልኅርስት ፓርክ ክርስታል ፓላስን በሚገጥምበት ጨዋታ ላይ እንደሚደርስ ተጫዋቹ  ተነግሯል፡፡

ቼልሲ በሊጉ ካስቆጠራቸው 12 ግቦች 6ቱን ማስቆጠር የቻለው ስፔናዊው የ24 አመቱ አጥቂ ዛሬ በኢንስታግራም አካውንቱ ላይ“ለሽንፈት ጊዜ የለኝም ለማገገም በሚገባ እየሰራው ነው” በማለት ከጎኑ የክርስታል ፓላስን ኢሞጂን በመለጠፍ በፍጥነት ከጉዳቱ ለማገገም እየተጋ መሆኑን ጽፏል፡፡

የ24 አመቱ አልቫሮ ሞራታ  ባሳለፍነው ሰኞ ወደ ስፔን አቅንቶ ጉዳቱ ከፍተኛ እንዳልሆነ እና ግፋ ቢል ለ4 ሳምንት ከሜዳ እንደሚያርቀው ቢነገረውም በግል የኢንስታግራም አካውንቱ ግን ከዚህ በቀን በፈጠነ መልኩ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ለደጋፊዎቹ አስደሳች የሆነ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም ሰማያዊዎቹ በቀጣዮቹ 5 ሳምንታት ውስጥ 7 ጨዋታዎችን በሁሉም ውድድሮች የሚያደርጉ ሲሆን በቻምፒየንስ ሊጉ ወደ ጣሊያን በማቅናት ሮማን እንዲሁም በወርሀ ህዳር መጀመሪያ በስታምፎርድ ብሪጅ ማንችስተር ዩናይትድን የሚገጥሙበት ጨዋታ ከወዲሁ በለንደኑ ክለብ ከፍተኛ ግምቱን ያገኘ ሆኗል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s