ክርስቲያኖ ሮናልዶ በብድን ጓደኞቹ ደስተኛ አይደለም

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሊዮ ሜሲ እያስቆጠረ ያለው የጎል ሪከርድ ላይ ለመድረስ የቡድን ጓደኞቹ እያገዙት ባለመሆኑ መከፋቱን አንድ የስፔን ሚዲያ ገልጿል።

በላሊጋው መልካም ጅማሮ ማድረግ ያልቻለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በስፔን ሱፐር ካፕ ላይ ዳኛን በመግፋቱ ለቅጣት ተዳርጎ ቆይቷል።

በተቃራኒው የባርሴሎናው ሊዮ ሜሲ በአስገራሚ የጎል ሪከርድ ከምንጊዜዉም የተለየ አጀማመር ማድረግ ችሏል።

ሜሲ በላሊጋው በ7 ጨዋታ 11 ጎል በማስቆጠር ሪያል ማድሪድ እንደ ቡድን በላሊ ካስቆጠረው ጎል ጋር ተቀራራቢ ሆኗል።

ይህ ደግሞ ለወትሮ ለሚፎካከረው ክርስቲናኖ ሮናልዶ ጥሩ ስሜት  የሚሰጥ ባለመሆኑ ፈጥኖ ጎሎችን እያስቆጠረ የቀድሞ ተፎካካሪነቱን ለመመለስ ይፈልጋል።

ነገርግን ይህን ለማድረግ አብረውት የሚገኙት የቡድን አጋሮቹ እገዛ እያደረጉለት ባለመሆኑ መከፋቱ ተሰምቷል።

እንደ ስፔኑ ዶን ባሎን መረጃ ከሆነ ተጫዋቹ ሊዮ ሜሲ ላይ ለመድረስ ኢስኮ እና አሴንሲዮ ለጎል የሚሆን ኳስ አመቻችተው እንዲያቀብሉት ቢፈልግም ይህን ግን በበቂ ሁኔታ ባለማግኘቱ ደስተኛ አለመሆኑን ነው የዘገበው።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s