የሌዢያ ቫርሳቫ ተጫዋቾች በገዛ ደጋፊዎቻቸው ጥቃት ደረሰባቸው 

የፖላንዱ ክለብ ለዢያ ቫርሳቫ ተጫዋቾች እሁድ ዕለት በፖላንድ ሊግ በለች ፖዝናን ክለብ 3ለ0 በመሸነፋቸው ምክኒያት በስታዲዮን ሚየስኪ አቅራቢያ በሚገኝ የመኪና ማቆሚያ አቅራቢያ በገዛ ደጋፊዎቻቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተዘግቧል። 

እንደፖላንዱ የህትመት ውጤት ፕርዘግላድስፖርታቪይ መረጃ ከሆነም ተጫዋቾቹና የክለቡ አሰልጣኞች ለመጓጓዧነት በሚጠቀሙበት አውቶቡስ ውስጥ እንዳሉ 50 በሚጠጉ በክለቡ ውጤት የተቆጡ ነውጠኛ ደጋፊዎች የድብደባና የስድብ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል።

እንደጋዜጣው ተጨማሪ ዘገባ ከሆነም በክለቡ የተጫዋችነት ዘመናቸው 200 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻሉትና አሁን ደግሞ ለክለቡ በረዳት አሰልጣኝናት እየሰሩ የሚገኙት አሌክሳንደር ቩኮቪች የደረስባቸው በጡጫ የመመታት ጥቃትን ጨምሮ በሌሎች ተጫዋቾች ላይም በጥፊ የመመታት ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

“ስትራች” የሚል ስያሜ ካላቸው እነዚህ ነውጠኛ ደጋፊዎች አንዱ ወደአውቶቡሱ በመግባት “በቀጣዩ ጨዋታም በተመሳሳይ መንገድ የምትጫወቱ ከሆነ ዳግመኛ እንመጣለን።” ሲል እንደዛተባቸውም የቡድኑን አባላት ሃሳብ እማኝ አድርጎ ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል። 

የቫርሳቫ ነውጠኛ ደጋፊዎች ባለፈው የካቲት ወር በአውሮፓ ህብረት እግርኳስ ማህበር የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ በሆላንዱ ክለብ አያክስ አምስተርዳም ደጋፊዎች ላይም ጥቃት ፈፅመው ነበር።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s