የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና የማናጀሩ ውዝግብ ቀጥሏል

ለአመታት የቀነኒሳ በቀለ ወኪልና ማናጀር በመሆን ሲሰሩ የቆዩት ጆስ ሄርማንስ በቅርቡ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን አትሌቱ አቋርጦ መውጣቱን አስመልክቶ የሰላ ትችት ሰንዝረውበት እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን ቀነኒሳም ለዚህ ትችት ያለውን ምላሽ አሳውቋል፡፡

ማናጀሩ ቀነኒሳ ብዙ ተጠብቆበትና ክብረወሰን እንደሚያሻሽል ተስፋ ተጥሎበት የነበረውን ውድድር ማቋረጡን ተከትሎ የአትሌቱ “ከፕሮፌሽናሊዝም” የራቀ የልምምድ ፕሮግራምና ልምድ ውጤቱን እንዳሳጣው ገልፀው በዚህ አኳኻኑም የቀድሞ ክብሩን ሊመልስና የማራቶንን ክብረ ወሰን መስበር የማይታሰብ እንደሆነ ተናግረው ነበር፡፡

ማናጀሩ ከቀነኒሳ በተጨማሪ ውድድሩን ማሸነፍ የቻለው ኬንያዊ ኢሉድ ኪፕቾጌ ማናጀርና ወኪል ሲሆኑ ሁለቱን አትሌቶች በማነፃፀር ኢትዮጵያዊውን ደንበኛቸውን ወርፈዋል፡፡

“ከአመታት በፊት በመም ውድድር ላይ ቀነኒሳ በተደጋጋሚ ኪፕቾጌን መርታት ችሏል ፤ አሁን ግን ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኗል፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ የፕሮፌሽናሊዝም ጉዳይ ነው፡፡ ኪፕቾጌ እስካሁን ካየዋቸው አትሌቶች ስራቸውን በሚገባ ከሚሰሩ የተለዩ አትሌቶች ከንዱ ነው” ያሉት ማናጀሩ አክለውም “ቀነኒሳ አትሊቲክሱንና የግለ ቢዝነሱን መለያየት እንጂ መቀላቀል የለበትም ” ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎ አትሌቱ በራሱ ሆቴል ከ LetsRun.com ጋር ባደረገው ቆይታ በማናጀሩ አስተያየት ደስተኛ አለመሆኑንና ጉዳዮቻቸውን በሁለቱ መሃል ብቻ ማስቀረት እንደነበረባቸው ተናግሯል፡፡ 
“ጆስ በንግግሩ በኔ ምክንያት ቁማር የተበላ ሰው መስሏል ፤ ነገር ግን ይህ ስፖርት ነው፡፡ አንዳንዴ ታሸንፋለህ አንዳንዴ ደግሞ ትሸነፋለህ፡፡”ብሏል፡፡

ማናጀሩ በሱ የማራቶን ፕሮፌሽናሊዝም ላይ ያነሱትን ጥያቄ አስመልክቶም “እንዴት በማራቶን ታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበ እንዲሁም የአለም የ5000 እና የ 10000 ሜትር ባለክብረወሰን አትሌት እንደዚህ አይነት ጥያቄ ሊነሳበት ይችላል?” በማለት በጥያቄ ምላሹን ሰጥቷል፡፡

አትሌቱ የበርሊን ማራቶንን ላለማጠናቀቁ በወቅቱ የነበረው ዝናብና ቅዝቃዜ የራሱ አስተዋፅኦ እንደነበረው የተናገረ ሲሆን በተደጋጋሚ በማናጀሩ ” በዚህ ውድድር ክብረ ወሰን ካላሻሻልክ መቼም ልታሻሽለው አትችልም እያለ ይነግረኞ ነበር ፤ ይህም ጫናና ጭንቀትን ፈጥሮብኛል ” ሲል ተናግሯል፡፡

ቀነኒሳ ጨምሮም ከበርሊን ማራቶን በፊት ከጆስ ሄርማንስ ጋር ሊፈቱት የሚገባ ጉዳይ የነበረባቸው ቢሆንም ሳይፈቱት ወደውድድሩ ማምራታቸውን ተናግሯል፡፡
“ሁል ጊዜ የኔን የልምምድ ፕሮግራም ማወቅ ይፈልግ ነበር፡፡ የኪፕቾጌን ግን አያውቅም፡፡ ሁሌም የኔን ፕሮግራም ማወቅ እንደፈለገ እጠይቀዋለሁ፡፡አንድም ቀን ሰጥቼው አላውቅም፡፡ በዚህ ብስጭት ውስጥ ገብቶ ይሆናል” ያለው ቀነኒሳ አያይዞም የማራቶንን ክብረ ወሰን እጁ ለማስገባት እርግጠኛ እንደሆነና ያንን አሳክቶ የተጠራጣሪዎችን አፍ እንደሚያዘጋ ተናግሯል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s