ጉዳት / ሮሜሉ ሉካኩ በጉዳት ከቤልጄም ብሔራዊ ቡድን ጋር ልምምድ ሳይሰራ ቀረ

የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ በቁርጭምጭሚት ጉዳት የቤልጄም ብሄራዊ ቡድን የነበረው የሰኞው ልምምድ ላይ ባይሳተፍም የምርመራ ውጤቱ ግን ለአገሩም ይሁን ለክለቡ መልካም ዜና ሆኗል።

ከቀያይ ሰይጣኖቹ ጋር ድንቅ አጀማመር በማድረግ ጎሎችን እያመረተ የሚገኘው ግዙፉ ቤልጄማዊ አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ ከክለቡ ጋር የነበረው ያለፈው አርብ ልምምድ ጉዳት እንዳጋጠመው ተነግሮ ነበር።

ዩናይትዶች ክሪስታል ፓላስን ባስተናገዱበት የኦልድትራፎርድ ጨዋታ ላይ ላይሰለፍ እንደሚችል ከጨዋታው ጅማሮ በፊት ይወጡ የነበሩ መረጃዎች ቢያመለክቱም ቤልጄማዊው ተጫዋች ግን ሙሉ 90 ደቂቃ ለመጫወት በቅቷል።

በእለቱም እንደተለመደው አንድ ጎል በማስቆጠር የቡድኑ ሁነኛ ጎል አስቆጣሪ መሆኑን ቀጥሎበታል።

ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ለማድረግ የቤልጄም ብ/ቡድንን የተቀላቀለው ሉካኩ የጉዳቱ ስሜት ሙሉለሙሉ ባለመጥፋቱ የሰኞውን ልምምድ ማድረግ አልቻለም።

ተጫዋቹ በእለቱ ምርመራ በማድረግ ጊዜውን ያሳለፈ ሲሆን የምርመራ ውጤቱም ቁርጭምጭሚቱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማሳየቱ ለአገሩም ይሁነረ ለክለቡ የምስራች ሆኗል።

ከውጤቱ በኋላም “በቀጣዩ ቀን በግሉ ልምምድ ማድረግ ይጀምራል፣ለጨዋታው ዝግጁ አይደለም ለማለት አሁን ጊዜው አይደለም።”የሚል አስተያየት ከቤልጄም ብ/ቡድን ካምፕ ተሰምቷል።

ዩናይትዶች ከኢንተርናሽናል ጨዋታ በኋላ ላለባቸው የተጨናነነቀ የፕሪምየርሊግ እና የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ የተጫዋቹን አገልግሎት አጥብቀው ይመኙታል።

ከአንድ ሳምንት የክለቦች እረፍት በኋላ አንፊልድ ላይ ሊቨርፑልን በመግጠም የሚጀምሩት ዩናይትዶች ቤኒፊካን በቻምፕየንስ ሊግ እንዲሁም ስፐርስና ቼልሲም በቅርቡ የሚያገኟቸው ጠንካራ ቡድኖች በመሆናቸው ተጫዋቾቻቸው ከአገራዊ ግዴታ በጥሩ ጤንነት እንዲመለሱ ይፈልጋሉ።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s