ጉዳት / ሰርጂዮ አግዌሮ ለ 6 ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል

Sergio Aguero could be out for six weeks, according to reports in Argentina

ከባድ ሳምንት በጉዳት እና በቤተሰብ ጉዳዪች እያሳለፈ የሚገኘው ሰርጂዮ አግዌሮ ከ2 ሳምንት በኋላ ወደ ሜዳ ይመለሳል ቢባልም ከወደ አርጀንቲና በተሰማ ዜና ግን በትንሹ እስከ 6 ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ነው፡፡ የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ዶክተሮች ተጫዋቹን ከተመለከቱ በኋላ ከ6 ሳምንት በኋላ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ዶክተር ዶናቶ ቪላኒ እንዳሉት ከሆነም እርሱ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ወደ እዚህ መጥቶ ሀገሩን ማገልገል ባለመቻሉ በጣም ተጸጽቷል፡፡ አርጀንቲናን በአለም ዋንጫው የመጨረሻ ጨዋታዎች ላይ መርዳት ይፈልግ ነበር ሆኖም ጉዳቱ ለጊዜያት ከሜዳ የሚያርቀው በመሆኑ ያንን ማድረግ አልቻለም ፡፡ እርሱ ምን አልባትም እስከ 1 ወር ከ2 ሳምንት ወደ ሜዳ ይርቃል በዚህም ክፉኛ ተቨሳጭቷል ሲሉ የብሄራዊ ቡድኑ ዶክተር ለቲዋይሲ ስፖርት ተናግረዋል፡፡

ማንችስተር ሲቲ አስካሁን በዶክተሩ አስተያየት ዙሪያ ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጠ ሲሆን ምን አልባትም ዶክተሩ ያሉት እውን ከሆነ እና ግብ አዳኙ አርጀንቲናዊ ከተባለው ጊዜ ዘግይቶ ወደ ሜዳ ከተመለሰ ማንችስተር ሲቲ በደርሶ መልስ ከናፖሊ ጋር  ከሚያደርገው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ እና በህዳር ወር መጀመሪያ ወደ ኤሜሬትስ አቅንቶ አርሰናልን በሚያገኝበት ጨዋታ ተሰላፊ አይሆንም፡፡

አርጀንቲናዊው አጥቂ በውድድር ዘመኑ በ8  ጨዋታዎች ለማንችስተር ሲቲ 7 ግቦች ከመረብ ያገናኘ ሲሆን በ1939 በክለቡ የምንግዜም ኮከብ ግብ አግቢ ኤሪክ ብሩክ ተይዞ የነበረውን 177 ግቦች ለሲቲ በማስቆጠር ሪከርዱን መጋራት ችሏል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s