12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፊታችን እሁድ ሊጀምር ነው

በፈይሰል ኃይሌ | ማክሰኞ መስከረም 23፣ 2010 ዓ.ም

12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር የፊታችን እሁድ መስከረም 28፣ 2010 በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄድ ይጀምራል።

ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ክለቦችና ተጋባዥ የክልል ክለቦች መካከል ሲካሄድ የቆየው ውድድር ዛሬ (ማክሰኞ) ረፋድ በኢትዮጵያ ሆቴል የምድብ ድልድልና የጨዋታ መርሃ ግብሮቹ ይፋ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ድልድል

የከተማ ውድድሩ በ2000 ዓ.ም ካለመካሄዱ ውጪ በየዓመቱ አዲሱ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት እንደቅድመ ውድድር የአቋም መለኪያ ዝግጅት በማገልገል ለ11 ጊዜያት ያህል ከፍተኛ ፉክክር ሲከሄድበት ቆይቷል።

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በሚካሄደው ውድድር በምድብ አንድ የተደለደሉት ኢትዮጵያ ቡና፣ ደደቢት፣ አዲስ አበባ ከተማና ጅማ አባ ቡና የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን እሁድ መስከረም 28፣ 2010 ዓ.ም የሚያደረጉ ሲሆን፣ በምድብ ሁለት ላይ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አዳማ ከተማ፣ ኢትዮ ኤክትሪክና መከላከያ ደግሞ ማክሰኞ መስከረም 30፣ 2010 ዓ.ም ጨዋታቸውን እንደሚያከናውኑ የውድድሩ አዘጋጆች ገልፀዋል።

ለ12 ዓመታት ሲካሄድ የቆየውን የመዲናይቱ ከተማ የክለቦች ውድድርን ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአራት ጊዜያት ያህል በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና እና አምና ቅዱስ ጊዮርጊስን 1ለ0 ማሸነፍ የቻለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሶስት ሶስት ጊዜ በማሸነፍ ሲከተሉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል። 

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s