ሴስክ ፋብሪጋዝ በ2004 ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ላይ ፒዛ መወርወሩን አመነ


2004 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ በውዝግብ በተጠናቀቀው ጨዋታ ላይ የአርሰናልን የ 49 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ሪከርድ ሲገታ ከጨዋታው በኋላ በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ፊት ላይ ፒዛ የወረወረው ሴስክ ፋብሪጋዝ መሆኑን ከ 13 አመታት በኋላ አምኗል።

በ2003/2004 ሽንፈትን ሳይቀምሱ የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ዋንጫ ብዙዎቹን በአድናቆት አፍ አስይዘው የተሞሸሩት መድፈኞቹን የሽንፈትን ጽዋ ለመቅመስ 49 ጨዋታዎችን መጠበቅ ግድ ብሏቸው ነበር።

በአዲሱ የውድድር ዘመን በጥቅምት 2004 ላይ ግን የወቅቱ ባላንጣቸው ማንችስተር ዩናይትድ መድፈኞችን በኦልድትራፎርድ ሲያንበረክክ ጨዋታው በብዙ ውዝግቦች ታጅቦ እስከ መልበሻ ቤት ተጉዟል።

በተጫዋቾች ሹክቻ ታጅቦ የደስታ ስካር በቀያዮቹ ሰይጣኖች ኮሪደርና መልበሻ ቤት በደመቀበት ቅጽበት በታላቁ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ፊት ላይ ያረፈው ፒዛ እስካሁን ድረስ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

“የፒዛው ፍልሚያ”በተባለው ጨዋታ ከ 13 አመታት በኋላ በወቅቱ ወጣት የነበረው ሴስክ ፋብሪጋዝ በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ፊት ላይ ፒዛውን መወርወሩን አምኗል።

በወቅቱ ማርቲን ኪዎን ፒዛውን ፋብሪጋዝ እንደወረወረው ፍንጭ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻም ባለቤቱ እራሱ ድርጊቱን መፈጸሙን አምኗል።

ዩናይትዶች የተጋጣሚ ቡድን ከጨዋታ በኋላ እንዲመገቡ ፒዛ በመልበሻ ቤታቸው የማስቀመጥ ልማድ ነበራቸው።

አጋጣሚዉን ያስታወሰው ፋብሪጋዝ “በድንገት የጫጫታ ድምጽ ሰማው፣ምን እንደተፈጠረም ለማወቅ ፈለግኩ፤ስለዚህ ፒዛዬን ይዤ ወደ ውጪ ወጣው

“ሪዮ ፈርዲናንድ፣ካምቤል፣ማርቲን ኪዎን እና ሌሎችም ሲገፋፉ አየው እጄ ላይ የነበር ፒዛ እንዴት እንደወረወርኩት አላውቅም፣በቃ ወረወርኩት

“ማን ላይ እንዳረፈ ተመለከትኩ፣ሰር አሌክስ ፈርጉሰንን በእውነት ይቅርታ እጠይቃለው ያደረኩት ነገር አስቤው አልነበረም።” ሲል አስታውሷል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s