ቅጣት / ፊፋ ዛምቢያን ቀጣ

የፊፋ የስነምግባር ኮሚቴ አፍሪካዊቷ ዛምቢያ ላይ ቅጣት ማስተላለፉን አሳወቀ።

በፈረንጆቹ የቀን ቀመር መስከረም 2/2017 ላይ በናሽናል ሄሮ ስታድየም ዛምቢያ እና አልጄሪያ ያደረጉት ጨዋታ ላይ ደጋፊዎች ቁሳቁስ ወደ ሜዳ ሲወረውሩ ታይተዋል።

ባለሜዳዎቹ ዛምቢያዎች ምንም እንኳን ጨዋታውን ቢያሸንፉም ፋሽን ሳካላ በሁለት ቢጫ በወጣበት ቅጽበት ደጋፊዎች ውሳኔውን በመቃወም ጠርሙስ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ወደ ሜዳ በመወርወር ያልተገባ ባህሪ አሳይተዋል።

በዚህም መሰረት የፊፋ የስነምግባር ኮሚቴ ጉዳዩን ከተመለከተ በኋላ ዛምቢያ ላይ ማስጠንቀቂያ እና ቅጣት አስተላልፏል።

ፊፋ በመግለጫው በአንቀጽ 65 እና 66 የስታድየም ጸጥታ እና ጥበቃ መመመሪያ መሰረት ዛምቢያ ደጋፊዎቿ ያልተገባ ባህሪ በማሳየታቸው መቅጣቱን ገልጿል።ቅጣቱም ማስጠንቀቂያ ጨምሮ 10ሺ ዶላር እንደሆነ ታውቋል።

2013 ላይም በተመሳሳይ ዛምቢያ በሌቪ ምዋናዋሳ ስታድየም በደጋፊዎች ያልተገባ ስነምግባር በፊፋ 10ሺ ዶላር መቀጣቷ ይታወሳል።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s