ሹመት / ኮሎ ቱሬ የአይቮሪኮስት ብሄራዊ ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ተደርጎ ተሾመ

1

የቀድሞ የአርሰናል ኮከብ ኮሎ ቱሬ ጫማውን ከሰቀለ ከጥቂት ወራት በኋላ የአይቮሪኮስት ብሄራዊ ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል፡

 

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በተለይ በ 2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ በመድፈኞቹ ደጋፊዎች ከሚወደዱት ተጫዋቾች አንዱ የነበረው ኮሎ ቱሬ ወደ አዲሱ የአሰልጣኝነት ስራው ጫማውን ከሰቀለ ከጥቂት ወራት በኋላ መቀላቀል ችሏል፡፡

የቀድሞው ኮከብ ተጫዋች የሀገሩን አይቮሪኮስት ብሄራዊ ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ ከዋናው አሰልጣኝ ማርክ ዊልሞትስ በመቀጠል የብሄራዊ ቡድኑ ዋና ሰው ሆኗል፡፡

በዚህም መሰረት አይቮሪኮስት ከማሊ ጋር ለሚኖራት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ቱሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የብሄራዊ ቡድኑን ስራ በይፋ በመጀመር ቡድኑን መምራት የሚጀምር ይሆናል፡፡

ቱሬ በእንግሊዝ ለ 17 አመት መቆየት የቻለ ሲሆን ከአርሰናል እና ከማንቸስተር ሲቲ ጋር የፕሪምየርሊግን ዋንጫ ማንሳት ችሏል፡፡ከአይቮሪኮስት ጋር ደግሞ የ 2015 የአፍሪካ ዋንጫን አሸናፊ ሆኗል፡፡

2013 ላይ ብሬንዳን ሮጀርስ ተጫዋቹን በነጻ ዝውውር ወደ ሊቨርፑል ካመጡት በኋላ ለሶስት አመት ከቀዮቹ ጋር በመቆየት 71 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል፡፡ባለፈው አመትም ሴልቲክ የሶስትዮሽ ዋንጫን ሲያሸንፍ የቡድኑ አባል እንደነበር ይታወሳል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s