ባየርን ሙኒክ የቀድሞ አሰልጣኙን መልሶ ለመቅጠር ተስማማ


በቅርቡ አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲን ከኃላፊነት ያነሳው የባቫሪያኑ ክለብ በቀድሞው ጊዜ ለታላላቅ ክብሮች ያበቁትን አሰልጣኝ ለመቅጠር መስማማቱ ተሰምቷል፡፡

ክለቡ ለአራተኛ ጊዜ ወደሹመት ያመጣቸው አሰልጣኝ ዩፕ ሄይንክስ ሲሆኑ በ 2013 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግንና ቡንደስሊጋውን ጨምሮ ሶስት ዋንጫዎችን ማንሳት የቻለውን ድንቅ ስብስብ ለዓለም ካሳዩ በኋላ ራሳቸውን ከአሰልጣኝነት አግልለው እንደነበረ ይታወሳል፡፡

ጣሊያናዊውን ካርሊቶን ካሰናበተ በኋላ አሰልጣኝ ሀሰሳ ላይ የሚገኘው ሙኒክ ከቀድሞው የዶርትሙንድ አለቃ ቶማስ ቱቸል እና በርካታ ሌሎች አሰልጣኞች ጋር ስሙ እየተያያዘ ሲሆን የውድድሩን አመት ለመጨረስ ግን ሄይንክስን ምርጫው አድርጓል፡፡

በፓሪስ ሴንት ጀርሜይን የደረሰባቸውን ሽንፈት ተከትሎ የተቀዛቀዘውን የቡድን መንፈስ የማነቃቃት ኃሃፊነት የተጣለባቸው አሰልጣኝ ሄይንክስ በቡንደስሊጋው ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ክለብ ወደሻምፒዮንነት ማምጣት ግን ዋነኛ ስራቸው እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s