አቋም መፈተሻ/ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ማክስኞ ከሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል

Image result for ethiopian national team

ከጊዜ ወደ ጊዜ በውጤት አልባ መንገድ ላይ እየተጓዘ የሚገኘው የኢትዮጰያ ብሄራዊ ቡድን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2ኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ለማድረግ ወደ ሞሮኮ ሊያቀና መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ወደ በቦትስዋና የነጻነት ቀን ወደ ጋቦሮኒ አቅንቶ የቦትስዋና አቻውን የገጠመው ብሄራዊ ቡድኑ የፊታችን ማክሰኞ ራባት ላይ ከሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን ጋር ጨዋታውን ለማድረግ ቅዳሜ ወደ ሞሮኮ የሚያቀና ይሆናል፡፡

ይህ ጨዋታ ከቀናት በፊት በተለያዩ የብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ ችግሮች እና ሞሮኮ ኢትዮጵያ ወጪዋን በመቻል ወደ ራባት እንድትመጣ  ማለቷን ተከትሎ መሰረዙ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ ከሞሮኮ አቻው ጋር ባደረገው ውይይት መሰረት ሞሮኮ የዋልያውን ወጪ ለመቻል በመስማማቷ ብሄራዊ ቡድኑ ማክሰኞ መስከረም 30 ከሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን ጋር ይጫወታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ቅዳሜ ወደ ሞሮኮ ሲያቀና 14 ተጫዋቾችን ብቻ ወደ ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር እንደሚሄድ የተነገረ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ከብሄራዊ ቡድኑ የተቀነሱ ተጫዋቾችን መኖራቸውን ተከትሎ የደደቢቱ ሽመክት ጉግሳ እና የሲዳማ ቡናው አጥቂ ባዮ ገዛኸኝ ዋልያውን ተቀላቅለው ወደ ራባት ያመራሉ፡፡

,

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s