ኡራጋይ 2018/ ከ17አመት የኢትዮጵያ በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ፍርፌ አገኘ

Image result for under 17 women world cup image

በ2018 ኡራጋይ ለምታሰናዳው የአለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከኬንያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ተድልድሎ የነበረው የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴት ብሄራዊ ቡድን  ኬንያ ራሷን ማግለሏን ተከትሎ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡

በዚህ ወር አጋማሽ እንዲካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ይህ ጨዋታ ኬንያ ዝግጁ አይደለሁም ማለቷን ተከትሎ የተሰረዘ ሲሆን ካፍም ለኢትዮጵያ ፎፌ በመስጠት በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ውሳኔውን አሳልፏል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ሴቶች ክለብ ዋና አሰልጣኝ በሆነችው ሰላማዊት ዘርዓይ የሚመራው ታዳጊ ቡድኑ ካሳለፍነው ወር ጀምሮ በዝግጅት ላይ የሰነበተ ሲሆን ይህንን ጨዋታ አለማድረጉን ተከትሎም ኢንተርናሽናል ጨዋታውን ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ ጋር ለማድረግ ወርሀ ህዳርን መጠበቅ የግድ የሚለው ይሆናል፡፡

ታዳጊ እንስቶቹ  ከ2 አመታት በፊት በዚህ ውድድር በአሰልጣኝ አስራት አባተ እየተመሩ በማጣሪያው ብዙ ርቀት  ቢጓዙም ህልማቸው በጋና ብሄራዊ ቡድን መጨናገፉን ተከትሎ በ2016ቱ የአለም ከ17 አመት በታች ዋንጫ ላይ ሳይሳተፉ ቀርተዋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s