የቀድሞ የአርሰናል ተከላካይ የነበረው ማርቲን ኪዎን ኦዚል ከአርሰናል ጋር ስለመቆየቱ እርግጠኛ እንደማይሆን እና ከወዲሁም የተጨዋቹ ጭንቅላት ከአርሰናል ውጪ እንደሆነ ተናግሯል።
የመድፈኛቹ የአጥቂ አማካይ የሆነው ኦዚል እስካሁን ድረስ የኮንትራት ማራዘሚያ ባለፈረሙ ከክለቡ ጋር መቆየቱ የተረጋገጠ ነገር የለም።
ክለቡም ቀደም ብሎ የኮንትራት ማራዘሚያ ቢያቀርብም ተጨዋቹ ሊቀበለው ባለመቻሉ ድርድሩ ተቋርጦ በሁለቱ ወገን ዝምታ ሰፍኗል።
እንዲያውም ከሰሞኑ ተጫዋቹ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጆሴ ሞሪንሆ ጋር በድጋሚ ሊቀላቀል እንደሚችል አንዳንድ መረጃዎች አመላክተዋል።
የቀድሞ የአርሰናል የተከላካይ መስመር ተጫዋች የነበረው ማርቲን ኬዎንም ተጫዋቹ ላይ እየተመለከተ ያለው ፍላጎት አነስተኛ በመሆኑ ከወዲሁ ጭንቅላቱ ከክለቡ መውጣቱን ገልጿል።
ኦዚል ለአርሰናል በአራት ጨዋታዎች ብቻ በቋሚ አሰላለፍ መጀመር የቻለ ሲሆን በዩሮፓ ሊግም ክለቡን ወክሎ መጫወት አልቻለም።
ጉዳት ላይ እንደሆነ የተነገረው ጀርመናዊ አማካይ ከጉዳቱ ለማገገም በጂም ልምምድ ሲያደርግ የሚያሳዩ ምስሎች ከሰሞኑን ሲወጡ ታይተዋል።
ማርቲን ኬዎን የተጨዋቹ ላይ ደረሰ በተባለው ጉዳትም ጥርጣሬ እንዳደረበት እንዲሁም ተጫዋቹ ለወደፊት ከአርሰናል ውጪ ስለመጫወት እያሰበ እንደሆነ ነው ያሳወቀው።
Advertisements