ክርስቲያኖ ሮናልዶ የባሎን ዶር ሽልማቱን ለበጎ አድራጎት ለገሰ

የሪያል ማድሪዱ ኮክብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለአንድ የበጎ አድራጎት ተቋም የባሎን ዶር ሽልማቱን በስጦታ ለግሷል።

ፖርቱጋላዊው ዝነኛ ተጫዋች ለተቸገሩ ሰዎች እጁን በመዘርጋት ተግባሩ ይታወቃል።

ከዓመታት በፊትም በልግስና ከሚታወቁ ቀደምት አትሌቶች መካከል አንዱ ነው በሚል ስሙ ከዚያን ጊዜ አንስቶ በተደጋጋሚ በከፍተኛ ሁኔታ ሲነሳ ቆይቷል። አሁንም ሽልማቱን ለበጎ አድራጎት ተግባር በመለገስ ስሙ ዳግም ተነስቷል።

እንደስፔኑ ጋዜጣ ማርካ መረጃ ከሆነ የሪያል ማድሪዱ ልዕለ ኮከብ በ2013 የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል በሽልማት ያግኘውን የወርቅ ኳስ ሽልማት በሳምንቱ መጭረሻ በልግስና በለንደን ለጨረታ እንዲቀርብ አድርጓል።

እናም ይህ “ሜክ ኤ ዊሽ” ለተሰኘ የበጎ ምግባር ተቋም በልግስና የተሰጠው ሽልማት ለጨረታ ቀርቦ አይዳን ኦፈር በተሰኛ እስራኤላዊ ባለሃብት በ530,000 ፓውንድ ዋጋ ተገዝቷል።

ሮናልዶ ሽልማቱን በስጦታ የሰጠው የእርዳታ ተቋም በከፍተኛ የህመም ችግር ውስጥ የሚገኙ ታማሚ ህፃናትን ለመርዳት የተቋቋመ ተቋም ነው።

በተያያዘ ዜናም ከክርስቲያኖ ሮናልዶ በተጨማሪ ሁለቱ የማንችስተር ከተማ አሰልጣኞች የሆኑት ፔፕ ጋርዲዮላና ሆዜ ሞሪንሆም በማንችስተር ከተማ የሚካሄድን የቦክስ ፍልሚያ ታድመው ለሚመለከቱበት የሚያገኙትን 26,000 ፓውንድ ክፍያ ለዚሁ ተቋም በእርዳታ ለግሰዋል።

የ32 ዓመቱ ሮናልዶ እንደሴቭ ዘ ቺልደረን፣ ዩኒሴፍ፣ ዎርልድ ቪዥን እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር ተሳትፎ ሲያደረግ ቆይቷል።

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነም ሮናልዶ በ2015 በኔፓል በመሬት መንቀጥቀጥ ምክኒያት 9,000 የሚደርሱ ሰዎች ከህልፈት ለተዳረጉበት ተፈጥሯዊ አደጋ 5 ሚ.ፓ ገንዘብ ለግሷል።

አጥቂው በቅርቡ በስፔን የታክስ መሰወር ተግባር ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ተከትሎ ሃብቱ ዝቅ ይላል ተብሎም ይጠበቃል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s