የላ ሊጋው ተጫዋቾች ወቅታዊው የውል ማፍረሻ ዋጋ 

ኔይማር ወደፒኤስጂ ባደረገው ዝውውር የዝውውር ውል ማፍረሻ ዋጋ የማደፈር ቁጥር እንዳልሆነ ማረጋገጫ ሆኗል። አሁንም ድረስ የአንዳንድ ተጫዋቾች የእብደት የሚመስሉ የውል ማሰሪያ ዋጋዎች እንዳይደፈር የሚያግዳቸው ነገር ያለ አይመስልም።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሪያል ማድሪድ ጋር ባለው የኮንትራት ስምምነት መሰረት ዋጋው 1 ቢሊዮን ዩሮ ነው። በሚደንቅ ሁኔታም ለሌላኛው በሪያል ማድሪድ የቡድን አጋሩ የሆነው ካሪም ቤንዜማም ዋጋው ተመሳሳይ መጠን አለው።

ባርሴሎና አዲስ ስምምነት በማስፈረም የሌዮኔል መሲ የውል ማፍረሻ ከፍ እንዲል ፍላጎት ቢኖረውም፣ አርጄንቲናዊው ተጫዋች አዲሱን ስምምነት ቢፈርም እንኳ ዋጋው ከ300 ሚ.ዩሮ ከፍ የማለቱ ዕድል ዝቅተኛ ነው። ይህ ማለት ደግሞ ከዓለማችን ምርጡ ተጫዋች በላይ ዘጠኝ የላ ሊጋ ተጫዋቾች የውል ማፍረሻ ዋጋ ይበልጣል ማለት ነው።

እንደስፔኑ ሊግ አስተዳዳሪዎች አባባል ከሆነ የሰራተኞች ህግ እያንዳንዱ ተጫዋች የውል ማፍረሻ አንቀፅ እንዲኖረው ያስገድዳል። ብዙውን ጊዜ ግን አንቀፁ የክለቦችን ጥቅም በማስከበር ላይ እንዲያመዝን ተደርጎ የወጣ ቢመስልም ከፍተኛ የውል ማፍረሻ ዋጋም “ተጫዋቹ የሚሸጥ አይደለም እንዳትሞክሩት፤ ጨርሶ እርሱት” የሚል መልዕክት እንዳለው ተደርጎ ይታሰባል። በሌላ ጎኑ ግን በአንቀፁ ላይ የሚነሳ ጥርጣሬያዊ ደንብ ክለቦች “ዕድላችሁን ሞክሩ። ተጫዋቹን ልንሸጠው እንችላለን።”  የሚል መልዕክት ያለው መሆኑ ነው።

ፒኤስጂዎችም የባርሴሎና እምቢተኝነት የቱንም ያህል ቢሆን እንኳ 222 ሚ.ዩሮ ቢያቀርቡ የኔይማርን ኮንታራት አቋርጠው ሊገዙት እንደሚችሉና ማንም ምንም ነገር ሊያደረግ እንደማይችል ጠንቅቀው ያውቁ ነበር።

በአንፃሩ ግን ባርሴሎና ባለፈው ክረምት ፊሊፔ ኮቲንሆን ለማስፈረም ወደሊቨርፑል ሲያመራ በዒለማቸው ውስጥ ያስገቡትን የህልም ዓለም ተጫወቻቸውን ለመግዛት የሚያስችላቸው ይህ ነው የሚባል የተረጋገጠ ዋጋ እንደሌለ ያውቁ ነበር።

ይህ ደንብ በስፔን እግርኳስ ላይ ትልቅ ፍሪዳ ቢሆንም ወደፕሪሚየር ሊጉ ሲመጣ ግን ተጫዋቾችን ኮንትራታቸውን እንዲያፈረሱ ሊያግዛቸው የሚያስችል የውል ማፍረሻ አንቀፅ የለም።

ብዙዎች አሁንም ድረስ ባርሴሎና ለኔይማር ያስቀመጠው 196 ሚ.ፓ (222 ሚ.ዩሮ) የውል ማፍረሻ ዋጋ ጣሪያ የሚደፈር እንደሆነ እምነቱ አላቸው። ምክኒያቱም ይህን ያህል ብቃት ያለውን ተጫዋቻቸውን ቢያጡ እንኳ በፋይናንስ ትርፍ ድርሻው ምክኒያት ያን ያህልም ኪሳራ አይሆንባቸውም።

አንዳንድ ጊዜ ተጫዋቾች መልቀቅ በፈለጉበት ሰዓት መልቀቅ ይችሉ ዘንድ ቀዳዳ ለማበጀት ሲሉ  ክለቦቹ ከሚፈልጉት ዋጋ በታች የውል ማፍረሻ አንቀፅ እንዲያዘጋጁ በክለቦቹ ላይ ግፊት ሊያደረጉ ይችላሉ።

በስፔን ላ ሊጋ በተጫዋቾቹ ኮንትራቶቹ ላይ የሰፈሩ 10 ውድ የውል ማፍረሻዎችም የሚከተሉትን ይመስላሉ።

ሮናልዶ – 1 ቢ.ዩ  (886ሚ.ፓ)

ሮናልዶ ያለጥርጥር የሚሸጥ ተጫዋች አይደለም። ሮናልዶ ከፈረመበት ጊዜ አንስቶም የውል ማፍረሻ አንቀፁ በዚሁ መንገድ ዘልቋል።

በመሆኑም ማንኛውም ክለብ ተጫዋቹን ለመግዛት የሚደፍር አይመስልም።

ካሪም ቤንዜማ – 1 ቢ.ዩ (886ሚ.ፓ) 

ከሁሉ በላይ “የማይሸጥ” የሚል ምልክት የተለጠፈበት ተጫዋች ነው። ምክኒያቱም ቤንዜማ ዋጋው 1 ቢ.ፓ የሆነ ተጫዋች ያለመሆኑ ግልፅ ነው።

It is virtually impossible to envisage any club spending ¿1bn on striker Karim Benzema

ኢስኮ፣ ማርኮ አሰንሲዮ – 700ሚ.ዩ (620ሚ.ፓ) 

ኢስኮ ውሉን ያደሰው ባለፈው ክረምት ነበር። እናም ሪያል ማድሪድ ምናልባት ባርሴሎና ኔይማርን ባጣበት መንገድ ላለማጣት ሲል 700 ሚ.ዩሮ ዋጋ ለጥፎበታል። 

ይህም በነዳጅ የናጠጡት ክለቦች በዚህ ዋጋ ተጫዋቹን ለማስፈረም ጥረት እንዳያደርጉ የሚያግዳቸው ነገር አለመኖሩ ጥርስ አልባ ለሚመስለው የስፔን የእግር ኳስ ሊግ አመራር አካል የማንቂያ ደውል ነው።

ነገር ግን እነዚህ አንቀፆች በፒኤስጂም ሆነ በየተኞቹም ክለቦች በጀት የሚደፈሩ አይደሉም።

Real Madrid are guarding their young talent such as Isco

Marco Asensio is another top young Spanish player

ጋርዝ ቤል፣ ሉካ ሞድሪች፣ ቶኒ ክሩዝ፣ ዳኒ ሲባሎስ – 500 ሚ.ዩ (443ሚ.ፓ) 

ቤል ኮንትራቱን ያደሰው በ2016 ነበር። ምንምእንኳ የውል ማፍረሻው ከሮናልዶ በግማሽ ቢያንስም ለየትኛውም ሸማች ክለብ ግን ዋጋው ውድ ነው።

በእርግጥ የውል ማፍረሻ አንቀፅ የማይደፈር ሊሆን ይገባል። ተጫዋቹን ክለቡ ሊሸጠው የማይፈልግ ከሆነም ዓላማቸውን በሚገባ አሳክተዋል ማለት ነው። 

የሶስቱ አማካኞች ዋጋ ምን ያህል ለሪያል ማድሪድ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ስኬት አይነተኛ ሞተር እንደነበሩ ይናገራል። ካባሎስም ለማድሪድ ዕጣ ፈንታ አብይ አካል ሆኖ ተቀለቅሏቸዋል።

Gareth Bale is among a number of Real players with ¿500m transfer release clauses

ኦስማኔ ዴምብሌ- 400ሚ.ዩ (354ሚ.ፓ) 

ባርሴሎና ዴምቤሌን ሲያስፈርም ፒኤስጂ ኔይማርን በ222 ሚ.ዩሮ ያስፈረመበት ስምምነት ቀለም አልደረቀም ነበር። በዚህም በስምምነቱ ላይም ከፍተኛ የውል ማፍረሻ አንቀፅ የማይሰፍርበትም ምንም ዓይነት መንገድ አልነበረም። 

Barcelona are protecting Ousmane Dembele with a huge release clause after losing Neymar

ሊዮኔል መሲ – 300ሚ.ዩ(266ሚ.ፓ) 

ባርሴሎና መሲ ክለቡን እንደማይለቅ እምነት አለው። እናም ምንም እንኳ የውል ማፍረሻ አንቀፁ በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ቢሆንም ተጫዋቹ በእነዚህ የክለቡ ቆይታ ዘመናቶቹ የገነባው ቁርኝት 300 ሚ.ዩሮ በጠረጴዛ ላይ ቢቀርበለት እንኳ ፈፅሞ ወደሪያል ማድሪድ ለማምራት አይጣደፍም።

ይህ ንድፈሃሳብ ብቻ ነው።  እናም አንዳንድ ስሜታዊ ደጋፊዎች የውል ስምምነቱ ከፍ ማለቱ አሁንም ድረስ ያስደስታቸዋል። በመሆኑም በሚቀጥለው ዓመት በነፃ እንኳ ሊለቅ የሚችል በመሆኑ አዲስ ኮንትራት እስኪፈርም ድረስ ይበልጥ የሚያሳስባቸው ጉዳይ ነው። 

Lionel Messi's contract says he is available for ¿300m - but the reality is probably different

ልዊስ ስዋሬዝ፣ ሰርጂዮ ቡስኬት፣ ጄራርድ ፒኬ፣ አንድሬስ ኢንየስታ፣ አንቶኒ ግሪዝማን – 200ሚ.ዩ (177ሚ.ፓ)

የስዋሬዝ የውል ማፍረሻ በተወሰነ መልኩ ከመሲ በታች ነው። 30 ዓዓመት ዕድሜ ላለውም ተጫዋች ክለቦች  ይህን ያህል ከፍተኛ ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ አይሆኑም። ኢንየስታ ደግሞ በሚቀጥለው ክረምት ከኮንትራት ነፃ ይሆናል።

የግሪዝማን የውል ማፍረሻ 100 ሚ.ዩሮ ቢሆንም ባለፈው ተዝውውር መስኮት ከፍ ብሏል። ምክኒያቱም አትሌቲኮ ማድሪድ በቅጣት ምክኒያት የእሱን ምትክ መግዛት አይችልም። በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ግን ወደ100 ሚ.ዩሮ ይመለሳል።

በወቅታዊው የዝውውር ሁኔታ ይህ በእጅጉ ዝቅ ያለ ዋጋ ነው። በመሆኑም የማይለወጥ ከሆነ ክለቡን ሊለቅ ይችላል ብሎ መጠበቅ ይቻላል። እርግጥ ነው ክለቡ የውል ማፍረሻ ስምምነቱን ከፍ የማድረግ ፍላጎት የሚኖረው ከሆነ ደመወዙንም ከፍ ማድረግ ይጠበቅበታል። 

Luis Suarez's is available for less than it cost PSG to buy his former team-mate Neymar

Atletico Madrid need to up Antoine Griezmann's release clause if they want to keep hold of him

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s