ባየር ሙኒክ የፕ ሄይክስን እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ በአሰልጣኝነት መቅጠሩን በይፋ ገለፀ

ባየር ሙኒክ የቀድሞ አሰልጣኙን የፕ ኬይንክስን እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ክለቡን በአሰልጣኝነት እንዲመሩ መቅጠሩን በይፋ ገልፅዋል። 

ሄይንክስ ከወጡበት የአሰልጣኝነት ጡረታ በመመለስ ባየር ሙኒክን ለአራተኛ ጊዜ የሚያሰለጥኑም ይሆናል።

ባየር ሙኒክን በ2013 የሶስትዮችሽ ዋንጫ ማንሳት እንዲችል ካደረጉት በኋላ የአሰልጣኝነት ስራቸውን አቁመው የነበሩት የ72 ዓመቱ ሰው ባለፈው ሳምንት የተሰናበቱትን ካርሎ አንቸሎቲን ተክተው በአሌያንዝ አሬና እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ የሚቆዩም ይሆናል።

“በዓለም ላይ ወደየትኛውም ክለብ አልመለስም ነበር። ነገር ግን ባየር ሙኒክ ከእኔ ጋር የፍቅር ቁርኝት አለው።” ሲሉ ሄንክስ ዳግመኛውን የባየር ሙኒክ የአሰልጣኝነት ቅጥራቸውን አስመልክተው ተናግረዋል።

ባየር ሙኒክ በአሁኑ ጊዜ ቡንደስሊጋው የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ ከሚገኘው ዶርትሙንድ በአምስት ነጥቦች ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን፣ በፒኤስጂ የ3ለ0 ሽንፈት ከደረሰበት በኋላ ለሻምፒዮንስ ሊጉ ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ዙር ለማለፍ እየታገለም ይገኛል።

ጀርመናዊ አሰልጣኝ፣ ሄይንክስ እ.ኤ.አ. በ2009 ዳግመኛ ተመልሰው ባየር ሙኒክን በጊዜያዊነት ከማሰልጠናቸው በፊት በክለቡ ለመጀመሪያ ጊዜ አሰልጣኝ ሆነው የተቀጠሩት እ.ኤ.አ. በ1987 ነበር። ከ2011-13 በክለቡ ረጅም ጊዜ መቆየት የቻሉበት የመጨረሻው የአሰልጣኝነት ዘመናቸው እህል ውሃ የተቋረጠው ደግሞ ክለቡ የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫና የሃገሪቱን የሊግ ናዋንጫ ውድድሮች አሸናፊ ከሆነ በኋላ ነበር።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s