አርጄንቲናና ቺሊ ወደዓለም ዋንጫ ማለፍ ይችሉ ይሆን?

በደቡብ አሜሪካ ለ2018 የሩሲያው ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገው ፉክክር አንድ የመጨረሻ ጨዋታ ብቻ ቀርቶታል። እናም በሰኔ ወር በሚካሄደው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ውድድር ላይም አርጄንቲናን ላናያት እንችላለን። ላ አልቢሴሌስቴዎቹ ከ ላ ቦምኖኔራዎቹ ጋር በቦነስ አይረስ ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ አርጄንቲና ወደሩሲያ ለማምራት የሚረዳትን ትኬት የምትቆርጥበት ዕድል በጣም አነስተኛ ሆኗል።

በ2014 የዓለም ዋንጫ እና ባለፉት ሁለት የኮፓ አሜሪካ ውድድሮች ላይ በሁለተኝነት ያጠናቀቀችውን ሃገር በየአራት ዓመቱ በሚደረገው ውድድር ላይ መለልከት አለመቻል የማይታለም ነገር ነው።

ከአርጄንቲና የማለፍ አጣብቂኝ ውስጥ የመግባት ሁኔታ በተጨማሪ በሚቀጥለው ሳምንት የሚደረጉር የኮንፌዴሬሽኑ የመጨረሻው የማጣሪያ ጨዋታዎች በእያንዳንዱ ሃገራት ቡድኖች የማለፍ ዕድል ላይ ምን ዓይነት አስተዋፅኦ ይኖረው ይሆን?

የደቡብ አሜሪካ ማጣሪያ 10 ሃገራት ብቻ የሚሳተፉበት እንደመሆኑ ከሌሎቹ እንደአውሮፓ እና አፍሪካ ካሉት ማጣሪያዎች ጋር ሲነፃፀር ልዩነት አለው።  በዚህ መሰረትም እያንዳንዱ ሃገራት እርስበርሳቸው ሁለት ጊዜያት (በሜዳቸውና ከሜዳቸው ውጪ) ተገናኘተው ይጫወታሉ። ይህ ደግሞ በድምሩ አንድ ሃገር 18 ጨዋታዎችን እንዲጫወት ያስገድደዋል ማለት ነው።

በዚህ አህጉራዊ የማጣሪያ ውድድር እስካሁን 17 ጨዋታዎች ተደርገዋል። ቀሪው ደግሞ አንድ ጨዋታ ብቻ ነው። እስካሁን በተደረጉት ጨዋታዎች መሰረትም የእያንዳንዱ ቡድን ነጥብ እና ደረጃ ይህን ይመስላል።

ብራዚል ማለፏን ያረጋገጠችበት የደ.አሜሪካ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የደረጃ ሰንጠርዥ

አሁን ባለው የደረጃ ሁኔታም በሁሉም የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ መሳተፍ የቻለችው ብራዚል ከወዲሁ ማለፏን አረጋግጣለች። ኢኳዶር፣ ቦሊቪያና ቬንዙዌላ ደግሞ ከማጣሪያው የደረጃ ሰንጠረዥ ወገብ በእጅጉ ዝቅ ብለው በመገኘታቸው ምክኒያት የማለፍ ዕድሉ የማይኖራቸው ሃገራት ናቸው። 

ኡራጓይ በአሁኑ ጊዜ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ብትገኝም የማለፏ ሁኔታ ግን ጨርሶ አርግጥ አልሆነም። ይሁን እንጂ ቢያንስ እስከአምስት ባለው ደረጃ ውስጥ ማጠናቀቅ መቻልዋን እርግጥ ሆናለች። ይህም ማለት አምስተኛ ሆና ብታጠናቅቅ እንኳ በኦሺኒያ የእግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ማለፏን ካረጋገጠችው ኒው ዚላንድ ጋር በበይነ ኮንፈዴሬሽን የደርሶ መልስ ማጣሪያ በመጫወት የማለፍ ዕድሏን ትሞክራለች።

በመጨረሻው ጨዋታ የመጨረሻ ሶስት አላፊ ቡድን ውስጥ ገብቶ ለማጠናቀቅ የሚደረገው ፍልሚያ በቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ፔሩ፣ አርጄንቲናና ፓራጋይ መካከል ይደረጋል።

የደ.አሜሪካ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታዎች

ጥቅምት 1፣ 2009 ዓ.ም የሚደረግው የመጨረሻው 18ኛው የማጣሪያ ጨዋታ መርሃ ግብር ይህን ይመስላል።

– ብራዚል ከ ቺሊ (በሳኦ ፖሎ)

– ኢኳዶር ከ አርጄንቲና (በኩዊቶ)

– ፔሩ ከ ኮሎምቢያ (በሊማ)

– ኡራጓይ ከ ቦሊቪያ (በሞንቴቪዲዮ)

– ፓራጓይ ከ ቬንዚዌላ (በአሰንሲዮን)

ሁሉም ጨዋታዎች የሚደረጉት በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

እያንዳንዱ ቡድን ለማለፍ ምን ማድረግ ይኖርበታል?

በብራዚልና ቺሊ መካከል የሚደረገው ጨዋታ የመጨረሻውን የደረጃ ሰንጠረዥ ደረጃ የሚወስን ነው። ሴሌሳዎቹ ከቺሊ ጋር በሙሉ አቅማቸው ተጫወቱም አልተጫወቱ ያ ጥያቄ አይሆንም።

ቺሊ ከኤኳዶር ጋር ባደረገችው ጨዋታ በመጨረሻው ሰዓት በአሌክሲ ሳንቼዝ ግብ ከማሸነፏ በፊት ስድስተኛ ደረጃ ላይ ትገኝ ነበር። አሁን ግን በአንድ ጊዜ ደረጃዋን አሻሽላ በሶስተኛነት መቀመጥ ችላለች። ይህ ደግሞ ከቦሊቪያና ፓራጓይ ጋር ያደረጓቸውን ያለፉትን ጨዋታዎች ለተሸነፉት ላ ሮኻዎቹ መልካም የሚባል ውጤት ነው።

አርጄንቲና በ17ኛው ጨዋታ በገዛ ሜዳዋ ከፔሩ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ ውጤት ማጠናቀቋ የምድብ ማጣሪያውን በቀጥታ ማለፍ የምትችልበትን ዕድል አሳጥቷታል። 

በመሆኑም የማለፍ ዕጣ ፈንታዋ በእጇ ላይ አይገኝም። የቀደመው ውጤታቸው ሲታይ ደግሞ አርጄንቲና በኢኳዶር በገዛ ሜዳዋ 2ለ0 ተሸንፋለች።  የ2014 ዓለም ዋንጫን በሁለተኝነት ያጠናቀቀችው ሃገር የግድ ማሸነፍ ቢጠበቅባትም የፔሩና የኮሎምቢያ ጨዋታ ውጤትም በደረጀ ሰንጠረዡ ላይ የሚያመጣው ለውጥ የራሱ አስተወፅኦ ሊያደርግላቸው ይገባል።

ሁለቱ ሃገራት ደግሞ የግድ ሶስት ነጥብ ማግኘት ስለሚገባቸው አርጄንቲና ጨዋታዋን ብታሸንፍ ከፔሩ ወይም ከኮሎቢያ አንዳቸውን በልጣ መቀመጥ ትችላለች። 

ኮሎምቢያና ፔሩ በደረጃው ሰንጠረዥ ከአርጄንቲና በታች የምትገኘውን ፓራጓይን ውጤት በአይነቁራኛ መመልከትም ይጠበቅባቸዋል። ፓራጓይ የምታሸንፍ ከሆነ (ወይም ሁለቱ ቡድኖች አቻ ከወጡ) ከሁለቱ ቡድኖች አንዳቸው በላይ ሊያስቀምጣት ይችላል። እንዲሁም ላ አልቢሮኻዎቹ ከቬንዙዌላ ጋር የሚጫወቱ እንደመሆናቸው የአርጄንቲናን ሽንፈት ተጠቅመው የደርሶ መልስ ማጣሪያው ደረጃ (5ኛ) ላይ መጨረስም የሚችሉበት ዕድል አለ።

ግምቶች?

አሁን ላይ ሆኖ ይህ ይሆናል ብሎ ውጤቶቹን መገመት በእጅጉ ያስቸግራል። ሁሉም ቡድኖች በተመሳሳይ ሰዓት የሚጫወቱ እንደመሆናቸው ቡድኖች የሌሎችን ውጤት ተመርኩዘው የሚፈልጉትን ውጤት በማምጣት ማለፍ የሚችሉበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም። በመሆኑም በቀጣዩ ሳምንት የሚደረጉትን እነዚህን አጓጊ ጨዋታዎች መጠበቅ የግድ ይላል። ይሁን እንጂ የሃገራቱ የማለፍ ዕድል በቁጥራዊ ቀመር በመቶኛ ሲቀመጥ ይህን ይመስለል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s