አስገራሚ / በላፓዝ አየር ንብረት የተቸገሩት ብራዚላዊኑ ኮከቦች ኦክስጅን ተጠቅመዋል

Brazil players received oxygen after a 0-0 draw against Bolivia in La Paz - 11,900 feet above sea level (Pic: Twitter: @CBF_Futebol)

ብራዚል ወደ ላፓዝ አቅንታ ከቦሊቪያ ጋር 0-0 በተለያየችበት የ2018 የሩሲያው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ክዋክብቶቿ በከፍተኛው አየር ንብረት ክፉኛ ተቸግረው አምሽተዋል፡፡

4 ጨዋታዎች እየቀሯት ወደ አለም ዋንጫው መጓዟን ያረጋገጠችው ብራዚል እግር ኳሰኞችም ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በከባዱ የአየር ንብረት ምክንያት  ልክ እንደ ምግብ ኦክስጅን በግላቸው ተሰጥቷቸዋል፡፡

የአለማችን ውዱ ተጫዋች ኔይማርን ጨምሮ በርካታ ስመ ጥር ተጫዋቾቿን ወደ ቦሊቪያ ይዛ ያመራችው ብራዚል ከባህር ጠለል በላይ በ11.932 ከፍታ ቦታ ላይ በሚገኘው የላፓስ ከተማ ውስጥ ለበርካቶች ውጤት ይዞ መመለስ ቢዳግትም ቢጫ ለባሾቹ ግን 1 ነጥብ ይዘው በመመለስ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞዋቸውን አሳምረዋል፡፡

ኔይማር ጁኒየር ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በኢንስታግራም አካውንቱ ላይ በቦሊቪያ እግር ኳስን መጫወት አያዝናናም በማለት ሀገሪቱ ለሌላ ሀገር ዜጎች እግር ኳስን ለመጫወት ምቹ አለመሆንኗን አብራርቷል፡፡

ከዚህ ቀደም አርጀንቲና በላፓዝ  በ2010ሩ የደቡብ አፍሪካ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከቦሊቪያ ጋር  ተጫውቷ 6-0 በሆነ ውጤት የተሸነፈች ሲሆን የደቡብ አሜሪካ ሀያላን የእግር ኳሱ ሀገራትም ወደዚች ሀገር ሲያመሩ በአየር ንብረቱ ምክንያት ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s