አንድሬስ ኢንዬስታ በባርሴሎና ለመቆየት”የዕድሜ ልክ” ውል ፈረመ 

ከዣቪ ሄርናንዴዝ የክለቡ ስንብት በኋላ የካታላኑን ክለብ በአምበልነት እየመራ የሚገኘው የመሃል ሜዳ ጠቢብ አንድሬስ ኢንዬስታ በኑው ካምፕ እስከመጨረሻው የሚያቆየውን ስምምነት ፈርሟል፡፡

የነበረው የውል ስምምነት በዚህ የውድድር አመት መጨረሻ ይጠናቀቅ የነበረው ተጫዋቹ በባርሴሎና ጫማውን መስቀል እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ሲናገር የሚደመጥ ሲሆን ይህ ዕቅዱ ተሳክቶ እግር ኳስ መጫወት ለማቆም እስከሚወስንበት ጊዜ ድረስ የክለቡ ተጫዋች ሆኖ መቀጠል የሚያስችለውን ዕድል ማግኘት ችሏል፡፡

ክለቡ በይፋዊ ድረ ገፁ እንዳሳወቀው”ዛሬ አርብ አንድሬስ ኢንዬስታ በባርሴሎና ቀሪውን የጨዋታ ዘመኑን የሚያጠናቅቅበትን ውል ፈርሟል፡፡ ” ብሏል፡፡
የ 33 አመቱ አማካይ ክለቡን ከ 21 አመታት በፊት የተቀላቀለ ሲሆን በወቅቱም የ 12 አመት ታዳጊ ነበር፡፡ የአለምና የአውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮኑ ኢንዬስታ በባርሴሎና ቆይታው 30 ክብሮችን በማንሳት ከሊዮኔል ሜሲ ጋር በጥምረት በክለቡ ታሪክ በርካታ ድሎችን ያስመዘገበ ተጫዋች ሆኗል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s