“ወደ ቻይና ያመራሁት ለገንዘብ ስል ነው” – ኦስካር

2.jpg

ብራዚላዊው የቀድሞ የቼልሲ ተጫዋች የነበረው ኦስካር ሳይታሰብ ወደ ቻይና ያቀናበት ሂደት ብዙዎቹ ያላሰቡት ቢሆንም ተጫዋቹ ግን ለገንዘብ ሲል ቻይናን ምርጫው ማድረጉን ተናግሯል፡፡

ባለፈው አመት ጥር ወር ላይ 60 ሚሊየን ፓውንድ ወጥቶበት ወደ ቻይና በማቅናት ለሻንጋይ የፈረመው ኦስካር በወቅቱ ሌሎች የአውሮፓ ትላልቅ ቡድኖች ጭምር ፊርማውን ፈልገው እንደነር ያስታውሳል፡፡

ተጫዋቹ ወጣት በመሆኑ ወደ ቻይና ያቀናል ተብሎ ባይታሰብም የብዙዎችን ግምት ወደ ኋላ አስቀርቶ ምርጫውን ቻይና አድርጓል፡፡ዘጠኝ ወር በቻይና ቆይታ ያደረገው ኦስካር ምርጫውን ያደረገው ቤተሰብን በማሰብ ለገንዘብ ሲል እንደሆነ ነው የገለጸው፡፡

“ወደ እዚህ ለመምጣት ሳስብ ከራሴ የእግርኳስ ህይወቴ ይልቅ ስለቤተሰበ ብዙ ማሰብ ነበረብኝ ምከንያቱም በኔ በኩል ሌሎች የአውሮፓ ትላልቅ ክለቦች ጥያቄ አቅርበውልኝ ነበር፡፡ነገርግን ስለ ቤተሰቦቼ ማሰብ ስለነበረብኝ እንዲሁም ወጣት በመሆኔ ወደ አውሮፓ ወደፊት መመለስ ስለምችል ውሳኔውን ወስኛለው፡፡

“የወሰንኩት ውሳኔ ምንም ይሁን ምን ጥሩ እና መጥፎ ጎን ይኖረዋል፡፡ነገሩን ግልጽ ለማድረግ ወደ ቻይና ያቀናሁት ለገንዘብ ስል ነው፡፡አትሌቲኮ ማድሪድ ለመቀላቀል ተቃርቤ ነበር፡፡ሚላን እና ጁቬንቱስም ጥያቄ አቅርበውልኛል ነገርግን ወደ ቻይና ለማቅናት ችያለው፡፡ወጣት ስለሆንኩም ወደፊት ወደ አውሮፓ መመለስ እችላለሁ፡፡”በማለት ተናግሯል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s