ቅጣት/ የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ኮከብ ዋይኒ ሩኒ ማህበራዊ አገልግሎቱን መስጠት ጀምሯል

ባሳለፍነው ወር መጨረሻ ጠጥቶ በማሽከርከር ወንጀል ተከሶ የገንዘብ ቅጣት እና የ100 ሰዓት ማሕበራዊ አገልግሎት በአካባቢው እንዲሰጥ በፍርድ ቤት የተበየነበት የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ኮከብ ዋይኒ ሮኒ ቅጣቱን አሃዱ ብሎ መጀመሩ ተነግሯል፡፡ የ31 አመቱ እንግሊዛዊ አርብ ከሰዓት በቼሻየር አካባቢ በሚገኝ  መናፈሻ በመገኘት ለታዳጊ ወጣቶች ትምህርት ሰጥቷል፡፡

ከዚህ በተጫማሪም በመናፈሻው በመገኘት የተለያዩ የጥገና ስራዎች የሰራም ሲሆን ከእንዚህም ውስጥ አትክልት መንከባከብ እና የመናፈሻውን ወንበሮች አጽድቷል፡፡ የማንችስተር ዩናይትድ እና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አጥቂው በማህበራዊ አገልግሎት መስጠቱ እንዳልተከፋ እና እንደውም በዚህ ተግባሩ እየተዝናናበት እንደሆነም ዴይሊ ሚረር አስነብቧል፡፡

በመርሲሳይዱ ክለቡ በሳምንት 150 ሺ ፓውንድ የሚከፈለው ዋይኒ ሩኒ መጠጥ ጠጥቶ ማሽከርከሩን ተከትሎ ካሁን በኋላ መኪና እንዳይነዳ እግድ የተጣለበት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ማህበረሰቡን ለ100 ሰዓታት በማህበራዊ ስራ ያለምንም ክፍያ እንዲረዳም የቼሻየር ፍርድ ቤት ወስኖበት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን  ተጫዋቹም ከወዲሁ የ12 ሰዓታት ማህበራዊ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡

ዋይኒ ሩኒ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ “ለሆነው ሁሉ ይቅርታ እጠይቃለው የፍርድ ቤቱንም ውሳኔ ተቀብያለው” እንዳለ የሚታወስ ነው፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለም እስካሁን ከዝነኛዋ ባለቤቱ ኮሊን 3 ልጆች የተበረከተለት ዋይኒ ሩኒ 4ኛ ልጅ አባት ሊሆን እንደሆነ ዲይሊ ሚረር ዘግቧል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s