በጫና ውስጥ የምትገኘው ክሮሺያ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኟን አሰናበተች

ክሮሺያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወሳኝ ጨዋታ ለማደረግ ሁለት ቀናት ብቻ እየቀራት የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኟን አንቴ ካቺችን በማሰናበት በምትካቸው ዝላትኮ ዳሊችን ቀጥራለች።

ቼክ አርብ ዕለት ከፊንላንድ ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቋ የካቺች የመጨረሻ ጨዋታ መሆኗ ማረጋገጫ ሆኗል።

ውጤትም ክሮሺያ ቱርክን ከሜዳዋ ውጪ 3ለ0 ካሸነፈችው አይስላንድ በሁለት ነጥቦች ዝቅ ብላ ወደሁለተኛ ደረጃ እንድትንሸራተት ምክኒያት ሆኗል።

ይህ ደግሞ በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ሰኞ የምድቡ መሪ አይስላንድ ኮሶቮን የምትገጥም በመሆኗ  የክሮሺያን ወደሩሲያ 2018 በቀጥታ የማለፍ ዕድል ዝቅ እንዲል አድርጎታል።

ክሮሺፓ ሰኞ በኪየቭ በምታደርገው ጨዋታ ሽንፈት የሚገጥማት ከሆነ ደግሞ የደርሶ መልስ ጥሎ ማለፍ ዕድልንም እንኳ ያለማግኘት አደጋ ተጋርጦባታል።

የክሮሺያ እግርኳስ ፌዴሬሽን (ኤችኤንአስ) የአሰልጣኝ ለውጥ ማድረጉን አስመልክቶ በይፋዊ ድረገፁ አማካኝነት በሰጠው መግለጫ የፌዴሬሽኑ ስራአሰፈፃሚ ቦርድ “ወቅታዊ ውጤቶችን” አንደምክኒያት አስቀምጦ ካቺችን ለማሰናበት “የመጨረሻው ውሳኔ” ላይ መድረሱን እና በምትካቸውም በአሁኑ ጊዜ የዩናይትድ አረብ ኤሚራትሱን ክለብ አል-አይንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙትን ዝላትኮ ዳሊችን በአሠልጣኝነት መሾሙን ገልፅዋል።

የ50 ዓመቱ ዳሊች ከዚህ ቀደም በክሮሺፓ ከ21 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ክፍል ውስጥ አገልግለው የሚያውቁ ሲሆን፣ ከ2010 አንስቶ አብዛኛውን የአሰልጣኝነት ጊዜያቸውን ያሳለፉት ግን በሳኡዲ አራቢያና በተባበሩት አራብ ኢሚራትስ ሃገራት ውስጥ ነበር።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s