ቶማስ ቨርማለን ህይወት በባርሴሎና እንደከበደው ተናገረ

የቀድሞ የአርሰናሉ የተከላካይ መስመር ተጫዋች የሆነው ቶማስ ቨርማለን በባርሴሎና እጅግ አስቸጋሪ ህይወት እየመራ እንደሆነ ተናገረ።

<!–more–>

በአርሰናል መልካም ቆይታ የነበረው ቤልጄማዊው ቶማስ ቨርማለን የለንደኑን ክለብ ከለቀቀ በኋላ ባሰበው መልኩ የተደላደለ ህይወት አልገጠመውም።

በባርሴሎና በጉዳት እንዲሁም የመጀመሪያ ተመራጭ አለመሆን ተጫዋቹ ከሜዳ እንዲርቅ አድርገውታል።

2016/2017 ላይ ባርሴሎና በቂ የመጫወት እድል እንዲያገኝ በውሰት ወደ ሮማ ልኮት ቆይቷል።ነገርግን ሮማ ዝውውሩን በቋሚነት ለመቀየር ፍላጎት ቢያሳይም የካታላኑ ቡድን ፍቃደኛ ሳይሆን የዝውውር መስኮቱ ተዘግቷል።

አሁን ተጫዋቹ በባርሴሎና ቢገኝም በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ሌላ ክለብ እንዳይዘዋወር ተደርጎ ለባርሴሎና ደግሞ ምንም አይነት የመጫወት እድል እየተሰጠው ባለመሆኑ አሳስቦታል።

ቨርማለን ጉዳዩ እጅግ ሀሳብ ውስጥ የከተተው ደግሞ ከተጠባባቂ ቡድን ጭምር ውጪ መሆኑ ህይወት በካታላን ጀርባዋን እንደሰጠችው ተረድቷል። 

በቤልጄም ብሔራዊ ቡድን ጭምር የመሰለፍ እድል የተነፈገው ቨርማለን ከአንድ የቤልጄም ጋዜጣ ጋር ቆይታ አድርጓል።

“ክለቡ በዝውውር መስኮቱ እንዳልዛወር አግዶኛል።ብዙ ክለቦች ቢፈልጉኝም እዚሁ ቀርቻለው።አሁን ከባርሴሎና ጋር ከሁለተኛ ቡድን ጋር እንኳን መጫወት ባለመቻሌ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እገኛለው።” በማለት ከባድ ህይወት እያሳለፈ መሆኑን ገልጿል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s