የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ነገ ይጀመራል

በአዲስ አበባ አግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰናጅነት የሚካሄደውና ስምንት ክለቦች የሚሳተፉበት የአዲስ አበባ ዋንጫ ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጀመራል፡፡

እያንዳንዳቸው አራት ክለቦችን በያዙ  ሁለት ምድቦች ተደልድለው የሚፉካከሩበት ውድድር በነገው ዕለት በምድብ “ሀ” ጨዋታዎች ሲጀመር ስምንት ሰዓት ላይ ደደቢት ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር የመክፈቻ ፍልሚያቸውን ያደርጋሉ፡፡

ውድድሩ ቀጥሎም ሌላኛው የምድቡ አባሎች ኢትዮጵያ ቡናና ጅማ አባ ጅፋር 10:00 ላይ እንደሚጫወቱ ፌዴሬሽኑ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አሳውቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ በተጨማሪም የስቴዲየም መግቢያ ዋጋዎችን ያሳወቀ ሲሆን ክቡር ትሪቡን 150 ብር ፣ ግራ እና ቀኝ ጥላፎቅ 100 ብር ፣ከማን አንሼ ወንበር ያለው 50 ብር ፣ ከማን አንሼ ወንበር የሌለው እንዲሁም ካታንጋ 20 ብር ፣ ሚስማር ተራ እና ዳፍ ትራክ 10 ብር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s