ዴል ፒየሮ “ልዕለ ኮከበ” ያለው ዲባላ በጁቬንቱስ እስከመጨረሻ የተጫዋችነት ህይወቱ መቆየት እንደሚችል ተናገረ

የጁቬንቱሱ ታሪካዊ ተጫዋች አሌሳንድሮ ዴል ፔየሮ የፓውሎ ዲይባላን አስደናቂ የውድድር ዘመን ጅማሮ አድንቆ፣ በክለቡ እስከመጨረሻው የተጫዋችነት ዘመኑ ድረስ የመቆየት አቅም ያለውን አርጄንቲናዊውን ተጫዋች “ልዕለኮከብ” ሲል ገልፆታል። 

ዲባላ በ2015 ከፓሌርሞ ጁቬን ከተቀላቀለበት ጊዜ አንስቶ ከዓለማችን ምርጥ አጥቂዎች አንዱ ለመሆን ትልቅ የሚባል መሻሻል እያሳየ ይገኛል፤ የውድድር ዘመን ጅማሮውም ከወዲሁ እጅግ መልካም ሆኖ ይገኛል።

የ23 ዓመቱ ተጫዋች ባለፈው የውድድር ዘመን ማስቆጠር ከቻለው 11 ግብ አንፃር ከወዲሁ ተሰልፎ መጫወት በቻለባቸው ሰባት የሴሪ ኣው ጨወታዎች 10 ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል።

እናም ዴል ፒየሮ አርጄንቲናዊው ልዕለ ኮከብ በጁቬ ደጋፊዎች ዘንድ ወደር የለሽ ተጫዋች እንደሆነ ያምናል።

“በዚህ የውድድር ዘመን ገና ከጅምሩ እንኳ ከነበረበት ደረጀ ከፍ ብሏል።” ሲል ዴል ፔሮ ለጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ተናግሯል።

“የሚያስደምሙ ተግባራትን እየፈፀመ ነው። እያወራሁ ያለሁት ስለግቦች አይደለም። እሱ ማድረግ ባለበት ሰዓት ውሳኔ ስለሚያሳልፍባቸው ጨዋታዎች ነው እየተናገርኩ ያለሁት። 

“እሱ እኔ በቱሪን ያደረግኩትን ነገር ማደረግ ይችላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ምክኒያቱም ማንም እንደእሱ በደጋፊው ልብ ውስጥ መግባት አይችልም። 

“10 ቁጥር መለያ በእርግጥም የእኔ ንብረት አልነበረም። ከእኔ በፊት ሮቤርቶ ባጂዮ፣ [ኦማር] ሲቮሪ እና [ሚሸል] ፕላቲኒም ለብሰውት ነበር።

“አሁን ደግሞ በጁቬ እንዳሻው እስከመጨረሻ ህይወቱ ድረስ ለመቆየት ሁሉ ነገር ያለው ልዕለኮከብ አለ። በዚህ ደግሞ እኔ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ።”

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s