ጉዳት / በኢንተርናሽናል ጨዋታ ማርዋን ፌሌይኒ ጉዳት አጋጠመው

የማንችስተር ዩናይትዱ አማካይ የሆነው ማርዋን ፌሌይኒ ቦስኒያ እና ቤልጄም ባደረጉት ጨዋታ ላይ ጉዳት አጋጥሞ ከሜዳ ተቀይሮ ወጥቷል።

ለ 2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ቦስኒያ እና ቤልጄም ባደረጉት የምሽቱ ጨዋታ ላይ ማርዋን ፌሌይኒ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ ወጥቷል።

ተጫዋቹ 20ኛው ደቂቃ ላይ በግራ ጉልበቱ ላይ ጉዳት ያጋጠመው ሲሆን ጨዋታውንም መቀጠል ሳይችል ቀርቷል።

ለ 2018 የአለም ዋንጫ ቀደም ብላ ማለፏን ያረጋገጠችው ቤልጄም የምሽቱን ጨዋታ የመርሀ ግብር ከማሟላት ውጪ ጥቅም የሚያገኙበት ጨዋታ አልነበረም።

የዩናይትድ ደጋፊዎች የዛሬ ሳምንት ከሊቨርፑል ጋር ላለባቸው ጨዋታ የፌሌይኒ ጉዳት ጥሩ ዜና አልሆነላቸውም።

ሉካኩም ጉዳት ላይ እንዳለ በተሰማበት ወቅት የፌሌይኒ ተጨማሪ ጉዳት ሌላ ተጨማሪ ጭንቀት ሆኖባቸዋል።

ተጫዋቹ ከዚህ አመት በፊት ጉዳት ሲያጋጥመው ትኩረት የሚሰጠው ባይኖርም አሁን ግን በቅርቡ እያሳየው በሚገኘው ጥሩ አቋሙ መሰረት ጉዳቱ ትኩረት አግኝቶ ደጋፊዎችንም ጭምር ሀሳብ ውስጥ ከቷል።

በዚህ መሰረት ዩናይትዶች በቀጣይ ቅዳሜ ሊቨርፑልን ሲገጥሙ የማቲች እና የሄሬራ ጥምረት በአማካይ ቦታ ላይ የመጠቀም እድላቸው የሰፋ ሆኗል። 

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s