ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ አትሌቶች የሚሳተፉበት የቺካጎ ማራቶን ነገ ይካሄዳል

የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤቱ ዴኒስ ኪሜቶና ጀግናዋ  የዓለም 5000 ሜትር ባለክብረወሰን ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ አትሌቶች ተሳታፊ የሚሆኑበት የቺካጎ ማራቶን ነገ ይካሄዳል፡፡

በውድድሩ  በሴቶች ጥሩነሽ ዲባባ ላለፉት ሁለት የስፍራው ውድድሮች ባለድል ከነበረችው ኬንያዊት ፍሎረንስ ኪፕላጋት ጋር የሚያደርጉት ፉክክር አጓጊ ሆኗል፡፡

በ 2014 የበርሊን ማራቶን 2:02:57 በመግባት ማራቶንን ከ 3 ደቂቃ በታች በመጨረስ ብቸኛው የሰው ልጅ መሆን ችሎ የነበረው ባለክብረወሰኑ ዴኒስ ኪሜቶ ከ 2015 የኒውዮርክ ማራቶን አሸናፊ የአገሩ ልጅ ስታንሊ ቢዎት ጋር ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ፤ የሪዮ ኦሎምፒክ የብር ሜዳልያ አሸናፊውና የአምናው የቶኪዮ ማራቶን ባለድል ፈይሳ ሌሊሳ ሌላኛው ተጠባቂ አትሌት ሲሆን ጠንካራው ኤርትራዊ ዘረሰናይ ታደሰም ከውድድሩ ተጠባቂዎች አንዱ ነው፡፡
የ 2009 እና የ2011 የዓለም የማራቶን ሻምፒዮኑ አቤል ኪሩይ የባለፈው አመት የቺካጎ ማራቶን ሻምፒዮን መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

በ  5000 እና 10000 ሜትር በኦሎምፒክና በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ፣ እንዲሁም በአለም አገር አቋራጭ ውድድሮች ታላላቅ ገድሎችን የፈፀመችው ጥሩነሽ ዲባባ ወደማራቶኑ ከመጣች በኋላ በወቅቱ ከሚገኙ ምርጥ የማራቶን አትሌቶች አንዷ መሆን የቻለች ሲሆን በእንግሊዛዊቷ ፓውላ ራድክሊፍ የተያዘውን ክብረወሰን የማሻሻል አቅም አላቸው ተብሎ ስማቸው ከሚያያዙ አትሌቶች ዋነኛዋ ናት፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s