ፍራቻ / እንግሊዛዊው የፖሊስ አለቃ ወደ ሩሲያ የአለም ዋንጫ ለሚሄዱ ደጋፊዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ

TELEMMGLPICT000100457051_trans_NvBQzQNjv4BqoQs0bxrJ0VMctHYmJMv0P08JefeBOfcHidgyq_sB56Qየአንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ወደ 2018ቱ የሩሲያው የአለም ዋንጫ ማለፉን ተከትሎ ከወዲሁ ብሄራዊ ቡድኑ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ እስከ 20 ሺ የሚጠጉ የብሄራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች ወደ ሩስያ ሀገራቸውን ለመደገፍ ይሄዳሉ በተባለበት በዚህ የአለም ዋንጫም ከወዲሁ የሩሲያዊያን ነውጠኛ ደጋፊዎች ጉዳይ በርካታ ተጓዦችን ያሳሰበ ሆኗል፡፡

ይህንን ተከትሎም የእንግሊዝ ብሄራዊ ፖሊሶች አለቃ የሆኑት ማርክ ሮበርትስ ወደ ሩስያ ለሚያቀኑ ደጋፊዎች ከወዲሁ ማስጠንቀቂያ አዘል አስያየት ሰጥተዋል፡፡

“ብሄራዊ ቡድኑን ለመገፍ የሚሄዱበት  ስፍራ የአደጋ ቀጠና ነው በ2016ቱ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ በማርሴይ ከፍተኛ የሆነ የደጋፊዎች ግጭት ተከስቶ ነበር፡፡ ለጸቡ መንስኤም ሩሲያዊኑ ነበሩ ስለዚህ አሁን ደግሞ እንግሊዛዊያኑ ወደ እዛ ያመራሉ በዚህ ምክንያትም ደጋፊዎች ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡ ”

“የማንችስተር ዩናይትድ እና የሊቨርፑል ደጋፊዎች ወደ ሩሲያ ሲያቀኑ እንዳደረጉት ሁሉ በርከት በሎ መጓዝ እና የብሄራዊ ቡድኑን መለያ አድርጎ በተናጠል አለመንቀሳቀስ ደግሞ አደጋውን ይቀንሰዋል” ሲሉ የፖሊስ አለቃው የመፍትሄ ሀሳባቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በሩሲያ የሚገኙ ነውጠኛ ደጋፊዎች ለአለም ዋንጫው ከወዲሁ ስጋት የሆኑ ሲሆን ከዚህ ቀደም በ2016ቱ የፈረንሳይ የአለም ዋንጫ ላይ ከእንግሊዝ እንዲሁም ከዌልስ ደጋፊዎች ጋር በስቴዲየም ጭምር ከፍተኛ ግጭት መፍጠራቸው የሚታወስ ነው፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s