አትሌቲክስ / ጥሩነሽ ዲባባ የቺካጎ ማራቶን አሸናፊ ሆነች

የሶስት ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነችው ጥሩነሽ ዲባባ የቺካጎ ማራቶን አሸናፊ ሆነች።

በውድድሩ ቅድሚያ ተሰጥቷት የነበረችው የአምና አሸናፊዋ ፍሎረንስ ኪፕላጋትን ብትሆንም የውድድሩን የመጨረሻ ሪባን መበጠስ የቻለችው ኢትዮጵያዊቷ ጥሩነሽ ዲባባ ነበረች።

ድንቅ ብቃት ያሳየችው ጥሩነሽ ዲባባ የገባችበት ሰአት 2:18:31 ሲሆን ኬኒያዊቷ ብሪጊድ ኮስጊ ሁለተኛ በመሆን ውድድሯን ስታጠናቅቅ የገባችበት ሰአት 2:20:22 ነበር።አሜሪካዊቷ ጆርዳን ሀሴይ ደግሞ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።

ጆርዳን ሀሴይ የገባችበት 2:20:57 በአሜሪካ ታሪክ ሁለተኛው ፈጣኑ የማራቶን ሰአት ሆኖ ተመዝግቦላታል።

ጥሩነሽ አንደኛ ሆና በማጠናቀቋ የ 100ሺ ዶላር ሽልማት ሲበረከትላት ሁለተኛ ለወጣችው ኮስጊ 75 ሺ ዶላር እንዲሁም ጆርዳን ሀሴይ 50ሺ ዶላር ተሸልማለች።

ከውድድሩ በኋላ የተናገረችው ጥሩነሽ”ይህ ሶስተኛ የማራቶን ሩጫዬ ነው።አሸናፊም ስለሆንኩ በጣም ተደስቻለው።ይህን ውጤት ለማስመዝገብም ጠንክሬ ሰርቼ ነበር።” በማለት ተናግራለች።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s