አ.አ ሲቲ ካፕ/ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ ተጀመረ

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲጀመር አዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያውን ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡

የምድብ “ሀ” መርሃ ግብሮችን በማካሄድ የተጀመረው ውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታውን በደደቢትና በአዲሰ አበባ ከተማ ፍልሚያ ያደረገ ሲሆን የከተማ መስተዳደር ክለቡ በእንዳለማው ታደሰ ብቸኛ ጎል ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል፡፡

ቀጥሎ የተካሄደው በደማቅ የደጋፊ ድባብ የታጀበው የኢትዮጵያ ቡናና የጅማ አባ ጅፋር ጨዋታ አሸናፊው ሳይለይ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ይህንን ተከትሎም አዲስ አበባ ከተማ ምድቡን በ 3 ነጥብ መምራት ጀምሯል፡፡

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዚህኛው ውድድሩ በየጨዋታው ኮከብ ተጫዋቾችን መርጦ የሚሸልም ሲሆን በመጀመሪያው ጨዋታ የአዲስ አበባ ከተማው ዳዊት ማሞ ተሸላሚ ሲሆን በቀጣዩ ጨዋታ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናው ክሪስዝስቶም ንታምቢ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s