ኦሊቪየ ዥሩ የፑሽካሽ ሽልማት የመጨረሻ ሶስት ዕጩ ዝርዝር ውስጥ ገባ

የአርሰናሉ አጥቂ ኦሊቪየ ዥሩ ከዴይና ካስቴላኖስ እና አስካሪኔ ማሱሉኬ ጋር በመሆን የ2017 የፊፋ የፑሽካሽ (የዓመቱ ምርጥ ግብ) ሽልማት የመጨረሻ ሶስት ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ መግባት ችሏል።

ከመስከረም 29፣ 2010 ዓ.ም በፊት በተሠበሰበ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ሶስቱ ተጫዋቾች ባስቋጠሯቸው ድንቅ ግቦች ለመመረጥ የቻሉ ሲሆን፣ ሌላኛው ቀጣይ ዙር የድምፅ አሰጣጥ ደግሞ በአዲስ መልክ ተጀምሯል። በእያንዳንዱ ዙሮች የተሰበሰቡ ድምፃች በጋራ ተደምረው በዚህ ወር አጋማሽ በሚዘጋጀው የሽልማት ስነስርዓት ላይ ተሸላሚ የሚሆነውን ተጫዋች  የሚወስኑም ይሆናማል።

ኦሊቪየ ዥሩ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በክሪስታል ፓላስ ላይ በቄንጥ ያስቆጠረው አስገራሚ (“ስኮርፒዮን ግብ”) ግብ በዚህ ዘርፍ የመጨረሻ ሶስት ዝርዝር ውስጥ መግባት የቻለ የመጀመሪያው ተጫዋች አድርጎታል።

ከዥሩ በተጨማሪ  በተከታታይ ዓመታት በዚህ ዝርዝር ውስጥ መግባት ከቻሉ የቬንዜዌላ ወጣት ተጫዋቾች መካከል አንዷ የሆነችው ዴይና ካስቴላስ በፌፋ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ በካሜሮን ላይ ከሜዳው አጋማሽ ርቀት በአስደናቂ ሁኔታ ማስቆጠር በቻለችው ግብ፣ እንዲሁም በዚህ ዝርዝር ውስጥ በመግባት ለሃገሩና ከግብ ጠባቂዎች ሁሉ የመጀመሪያው የሆነው ደቡብ አፍሪካዊው ኦስካሪኔ ማሱሉኬ ክለቡ ቦርካ ከኦርለንዶ ፓራይሬትስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ባስቆጠረው የመቀስ ምት ግብ በፑሽካሽ ሶስት የመጨረሻ የሽልማት ዕጩ ዝርዝር ውስጥ መግባት የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው።

የሽልማቱ የመጨረሻ አሸናፊን ለመለየት የሚደረገው የድምፅ አሰጣጥ እስከሽልማቱ ቀን (ጥቅምት 13፣ 2010 ዓ.ም) ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በተሰበስበው የደጋፊው ድምፅ አሸናፊ መሆን የቻለው ተጫዋች ሽልማቱን በታሪካዊው የለንደኑ ፓላዲየም የሚቀበል ይሆናል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s