የአፍሪካ ሃገራት የ2018 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ተስፋ

የአፍሪካ ዞን የ2018 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ እ.ኤ.አ. ህዳር 6 ይደረጋል።

ከወዲሁ ማለፋቸውን ያረጋገጡ: ግብፅና ናይጄሪያ 
እስካሁን ያልታወቁ  ተሳታፊዎች: 3 በቀጥታ አላፊዎች

የትኞቹ ሃገራት የሩሲያውን የዓለም ዋንጫ ተቀላቀሉ? የትኞቹስ የተሳትፎ ትኬት የመቁረጥ የተሻለ ዕድል አላቸው? እንዴትስ ተሳትፏቸውን ሊያሳኩ ይችላሉ? የሚሉትን ጉዳዮች አንድ በአንድ እንደሚከተለው ተመልክተናቸዋል።

አራቱ አራት ሃገራት ከሚገኙባቸው አምስት የአፍሪካ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድቦች አምስቱ የየምድቦቹ ቀዳሚ ሃገራት በቀጥታ አላፊ ይሆናሉ። ከዚህ ውጪ የአፍሪካ ሃራት የዓለም ዋንጫውን የሚቀላቀሉበት መንገድ የለም።

ምድብ 

ጊኒና ሊቢያ ከወዲሁ መውደቃቸውን ሲያረጋግጡ ቱኒዚያ ዲ.ኮንጎን በሶስት ነጥቦች ቀድማ የምድቡ መሪ ሆና ትገኛለች።

ህዳር: ቱኒዚያ ከ ሊቢያ እና ዲ.ሪ.ኮንኮ ከ ጊኒ 

ቱኒዚያ የበላይነቷን ለማረጋገጥ ሊቢያን በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ማግኘት የግድ ይላታል። ቱኒዚያ ሽንፈት የሚገጥማት ከሆነ ግን ዲ.ሪ.ኮንጎ ሁለትና ከዚያ በላይ ግብ ማስቆጠር ግድ ቢላትም የመካከለኛው አፍሪካዊቷ  ሃገር አላፊ ልትሆን ትችላለች። ወይም ቱኒዚያ 2ለ1 ብትሸነፍ እና ዲ.ኮንጎ 1ለ0 ብታሸንፍ ሁለቱም ቡድኖች በግብ እኩል በመሆን እርስ በእርስ በተደረገ ጨዋታ አሸናፊ የነበረችው ቱኒዚያ የምድቡ አላፊ ትሆናለች።

ምድብ ቢ 

ናይጄሪያ  ባለፈው ቅዳሜ ዛምቢያን በሜዳዋ በመርታት የምድቡ ቀዳሚ ሆና ማለፏን አረጋግጣለች። 

ምድብ 

አይቮሪ ኮስት በመጨረሻው ቀን ከምድቡ መሪ ሞሮኮ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቃ ትፋለማለች።

ምድቡን በአንድ ነጥብ የምትመራው ሞሮኮ ከሜዳዋ ውጪ በሁለተኛ ደረጃ ከምትገኘው አይቮሪ ኮስት ጋር በምታደረገው የመጨረሻው ቀን ጨዋታ ሽንፈት እንዳይገጥማት ብቻ በማድረግ የዓለም ዋንጫውን መቀላቀል ትችላለች፤ ሽንፈት የሚደርስባት ከሆነ ግን የማለፍ ዕድሉን ለአይቮሪ ኮስት አሳልፋ የምትሰጥ ይሆናል። 

ምድብ ዲ

ይህ ምድብ ፊፋ በጨዋታ መጭበርበር ምክኒያት ደ.አፍሪካና ሴኔጋል በቀጣዩ ወር ዳግም ጨዋታ እንዲያደረጉ ውሳኔ ያስተለለፈበት ምድብ ነው። በምድቡ ሴኔጋል ስምንት ነጥብ ሲኖራት፣ ቡርኪናፋሶና ኬፕ ቨርዴ ስድስት ስድስት ነጥቦች አላቸው። ከሴኔጋል ጋር ሁለት ቀሪ ጨዋታ የሚቀራት ደ.አፍሪካ ደግሞ በአራት ነጥብ በመጨረሻ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ህዳር, 6: ቡርኪና ፋሶ ከ ኬፕ ቨርዴ
ህዳር. 10: ደቡብ አፍሪካ ከ ሴኔጋል
ህዳር. 14: ሴኔጋል ከ ደቡብ አፍሪካ

ሴኔጋል: ወሳኝ በነበረው ጨዋታ ኬፕ ቨርዴን በማሸነፍ የምድቡ አናት ላይ መቀመጥ ችላለች። በሚቀጥለው ወር ቡርኪና ፋሶ እና ኬፕ ቨርዴ የሚያደረጉትን የመጀመሪያ ጨዋታ በአቻ ውጤት የሚያጠናቅቁ ከሆነ ሴኔጋል ወደሩሲያው የዓለም ዋንጫ አላፊ ለመሆን ከደቡብ አፍሪካ ጋር በምታደርገው የመጀመሪያ ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘት ይበቃታል። 

ቡርኪና ፋሶ:  ኬፕ ቨርዲን የግድ ማሸነፍና ሴኔጋል ያለፈውን ጨዋታ አይነት ከደቡብ አፍሪካ ጋር በአቻ ውጤት እንድትለያይ ተስፋ ታደርጋለች።  ከፍፃሜ ለመብቃት ደግሞ ከሴኔጋል ጋር ያላትን የአራት ግብ ልዩነት ማጣፈት የግድ ይላታል። 

ኬፕ ቨርዴ: ተስፋዋ በእጅጉ የጠበበ ነው። ቡርኪና ፋሶን የግድ በሰፊ ግብ ማሸነፍ እና ሴኔጋል ከደቡብ አፍሪካ ጋር በአቻ ውጤት እንድትለያይ ተስፋ ማድረግ፣ እንዲሁም ለመጨረሻ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ለመብቃትም የግድ ያለባትን የስምንት ግቦች ልዩነት ማጣፋት ይጠበቅባታል። 

ደቡብ አፍሪካ: ቀላል ነው — በሜዳዋ እና ከሜዳዋ ውጪ የግድ ሴኔጋልን ማሸነፍ የፊታችን ሰኔ ወር የሚደረገውን የሩሲያ የዓለም ዋንጫ እንድትቀላቀል ያደርጋታል።   

ምድብ ኢ

ግብፅ፡ በጣም በእጅጉ በባከነ ሰዓት እሁድ ዕለት ባስቆጠረችው ግብ አማካኝነት በኮንጎ ላይ በተቀዳጀችው  የ2ለ1 ድል የምድቧ አላፊ መሆኗን አረጋግጣለች። 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s