ጉዳት / የሽኮርዳን ሙስጣፊ ጉዳት አርሰናልን አሳስቧል

“የፊፋ ቫይረስ” እየተባለ የሚጠራው ኢንተርናሽል ጨዋታ መድፈኞቹንም በመጎብኘት ጀርመናዊው ሽኮርዳን ሙስጣፊ ቀላል የማይባልጉዳት እንዳስተናገደ ተነግሯል።

ጀርመን አዘርባጃንን 5-1 ባሸነፈችበት ጨዋታ የአርሰናሉ ተከላካይ ጉዳት አጋጥሞት 36ኛው ደቂቃ ላይ ሜዳውን ለመልቀቅ ተገዷል።

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ዮዋኪም ሎው ተጨዋቹ የጡንቻ መሰንጠቅ የሚመስል ጉዳት እንዳጋጠመው በመግለጽ ከጨዋታም ለረጅም ጊዜ ሊያርቀው እንደሚችል ገልጸዋል።

አርሰናሎች ኮሽሊኒ ቀደሞ ብለው በጉዳት ያጡት በመሆኑ ቅዳሜ ዋትፎርድን ሲገጥሙ ያለ ሁለት ወሳኝ ሁለት የመሀል ተከላካዮቻቸው የመጫወት ግዴታ ውስጥ ገብተዋል።

በዚህም መሰረት ሌላኛው የመሀል ተከላካይ ሮብ ሆልዲንግ በቋሚነት ጨዋታውን የመጀመር እድሉ የሰፋ ሆኗል።

ለመድፈኞቹ ሙስጣፊን በጉዳት ቢያጡም ኦዚል እና ዌልቤክ ደግሞ ወደ ልምምድ መመለሳቸው በተቃራኒው መልካም ዜና ሆኖላቸዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s