ምቾት/ አንቶንዮ ማርሲያን በማንችስተር ዩናይትድ ደስተኛ ነው

Image result for Anthony Martial

በሳምንቱ አጋማሽ ከወጡ ዜናዎች መካከል ፈረንሳዊው ኮከብ አንቶንዮ ማርሲያል ማንችስተር ዩናይትድን ለቆ ወደ የአሌክሲስ ሳንቼዝ ምትክ በመሆን አርሰናል ሊሄድ ነው የሚሉ ዜናዎች በስፋት ቢሰሙም የከተማው ክለብ ጋዜጣ የሆነው ማንችስተር  ኢቭኒንግ ኒውስ እንዳስነበበው ከሆነ የ21 አመቱ ኮከብ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ደስተኛ ነው፡፡

በውድድር ዘመኑ ጅማሮ ዳግም የተወለደው ኮከብ በቲያትር ኦፍ ድሪምስ መድመቁን የቀጠለ ሲሆን በ9 ጨዋታዎች ላይ 5 ግቦች አስቆጥሩ ተጨማሪ 5ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል የቻለ ሲሆን ከአምናው በተሻለ መልኩም በርከት ያሉ ጨዋታዎች ላይ ተሰላፊ እየሆነ ይገኛል፡፡

ማንችስተር  ኢቭኒንግ በዘገባው  ፈረንሳዊው ተስፈኛ ኮከብ ሕይወት በዩናይትድ ቤት እንደተመቸው እና በክለቡም ደስተኛ መሆኑን ታማኝ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል ያለ ሲሆን  በጥር ወርም በቲያትር ኦፍ ድሪምስን ለቆ ወደ አርሰናል እንደማይሄድ ጋዜጣው አክሎ ገልፅዋል፡፡

በሊጉ እስካሁን 4 ግቦችን ያስቆጠረው አንቶንዮ ማርሲያል በማንችስተር ዩናይትድ ቤት በፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ እየመራ በሚገኘው ሮሜሎ ሉካኩ ብቻ በግብ መጠን ይበለጣል፡፡ በግራ መስመር ላይ እየተሰለፈ የሚገኘው  አንቶንዮ ማርሲያል ቀያይ ሰይጣኖቹን በ2015 ከፈረንሳዩ ሞናኮ በ56 ሚሊየን ፓውንድ የተቀላቀለ ሲሆን በክለቡ የ2 አመታት ቆይታውም የፕሪሚየር ሊግ የኤፍ ኤካፕ እንዲሁም የኢሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን መሳም ችሏል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s