ስያሜ / በግብጽ የአንድ ትምህርት ቤት ስያሜ በመሐመድ ሳላህ ስም ተቀየረ

​ግብጽ ከ27 አመት በኋላ ወደ አለም ዋንጫው እንድትመለስ ትልቁን ሚና በተጫወተው መሐመድ ሳላህ ስም አንድ ትምህርት ቤት ስያሜውን ቀየረ።

ፍርኦኖቹ በአለም ዋንጫው ማጣሪያ ጋና፣ዩጋንዳ እና ኮንጎ ይገኙበት በነበረበት ምድብ አሸናፊ በመሆን ወደ አለም ዋንጫው መቀላቀላቸው አረጋግጠዋል።

የምድቡ ሌላኛው ጨዋታ ቅዳሜ ላታ የተካሄደው የዩጋንዳ እና የጋና ጨዋታ በአወዛጋቢ ሁኔታ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ለግብጾቹ በቀጣዩ ቀን ለሚያደርጉት ጨዋታ የምስራች ነበር።

ይህን አጋጣሚም ኮንጎን 2-1 በመርታት ወደ ራሺያ የሚወስዳቸውን ትኬት የቆረጡት ግብጾቹ ደስታቸውን በዋና ዋና አደባባይ መግለጽ ችለዋል።

ለዚህ ክብር እንዲበቁ ደግሞ ትልቁን ሚና የተጫወተው የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተሰላፊ የሆነው መሐመድ ሳላህ ሲሆን አጥቂው በወሳኙ ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በተለይም በመጨረሻ ደቂቃ ላይ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ትልቁን ሀላፊነቱን በሚገባ መወጣት ችሏል።

ግብጾችን ለዚህ ክብር በማብቃት የጀግንነቱን ድርሻ ለተወጣው መሀመድ ሳላህ ክብር የአንድ ትምህርት ቤት ስያሜ በሱ ስም ተለውጧል።

ትምህርት ቤቱ ተጫዋቹ የተወለደበት ቦታ የሚገኝ እና የተማረበት ሲሆን ለውጡንም በአካባቢው አስተዳዳሪ የሆኑት አህመድ ደይፍ ጭምር ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s