አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ / ዛሬ የተደረጉ የምድብ 2 የአዲስ አበባ ከተማ ጨዋታዎች ያለ ግብ ተጠናቀዋል

22366496_757783957763571_1029762306048241613_n

ከተጀመረ ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዛሬ ከሰዓት እና አመሻሽ ላይ 2 ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስቴዲየም ተደርጎበታል ፡፡ ግብ አልባ ሆኖ ሆኖ ባለፈው የ2ኛ ቀን ውሎውም  ሁለቱም ጨዋታዎች ያለግብ ተጠናቀዋል፡፡

በ9ሰዓት በተደረገው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ ጥቂት ተመልካች በስቴዲየም የታደመ ሲሆን ቀዝቀዝ ያለ ጨዋታም ታይቶበታል፡፡ ሁለቱ ክለቦችም በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸው ያለ ግብ ያጠናቀቁ ሲሆን የአዳማው ከነማ የመስመር አጥቂ ሱራፌል ዳኛቸው በጨዋታው ላይ ባሳየው መልካም የሚባል ብቃት የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተሸልሟል፡፡

11 ሰዓት በመጀመረው እና በርካታ ታዳሚያን በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተከታተሉት የምሽቱ 2ኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ ያለ ግብ ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡ የፈረሰኞቹ አዲሶቹ ፈራሚዎች አብደልከሪም መሀመድ እና ኢብራሂም ፎፋና ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብተው ለክለቡ የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ ባሳለፍነው አመት በፈረሰኞቹ ቤት መልካም ብቃቱ ያሳየው አማካዩ አብደልከሪም ዜኮ ደግሞ በምሽቱ ጨዋታ ኮከብ ተብሎ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ እና ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ስፖንሰር ባደረጉት 12ኛው የከተማ ዋንጫ ጨዋታ ነገ በምድብ 1 የሚገኙት ክለቦች መካከል በአዲስ አበባ ስቴዲየም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ደደቢት ከ ጅማ አባ ጅፋር በ9 ሰዓት እንዲሁም በ11 ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና እና ከአዲስ አበባ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s